English አፍሪካ

ኢትዮጵያዊቷ  የላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ  ሰላም ዘርዓይ ሆና  መቀጠሯ የላይቤሪያ አሰልጣኞችን “ለማንቋሸሽ”  እንዳልሆነ  ፕሬዝዳንቱ  ተናግረዋል!

👇

የካፍ ኢንስትራክተር አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ታዳጊ እና ዋና ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፣ የቅ/ጊዮርጊስ የሴቶች ቡድን እና የወንዶች ተስፋ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም አሁን  የላይቤሪያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዋና አሰልጣኝ መሆኗ ይታወሳል።

የላይቤሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ራጂ የካፍ ኢንስትራክተር አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ሰላም  የዋናው የሴት ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርገው መቅጠራቸው  የላይቤሪያ አሰልጣኞችን  ዝቅ በማድረግ አሊያም “ለማንቋሸሽ” አይደለም ሲሉ  ለሦስት ቀናት በሚቆየው እና ዛሬ በተጀመረው የኢንስራተሮች  የማጠናከሪያ ኮርስ ላይ በንግግር ጀመረዋል ።

ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት እኔም ሆንኩ  አሰልጣኞቻችን እና ኢንስትራክተሮቻችን በሰላም  የዳበረ ዕውቀት  ተጠቃሚ  በመሆናችን  ደስተኞችን ነን  ካሉ በኃላ  ኢትዮጵያዊቷን ለመቅጠር የወሰነው  ያላትን እውቀት እና ፍላጎት ለእኛም ባለሙያዎች ላይ የሚጠቅም ሆኖ  ስለተረዳን ነው ብለዋል።
ነገር ግን ይኸ ማለት “የእኛን አሰልጣኞች ብቃት ለመናቅ  ታስቦ እንዳልሆነ እና  አሰልጣኝ ሰላም በአፍሪካ አህጉር  ያላትን  ልምድ ለእኛም እያካፈለች እንደሆነ  ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት ሰጥተዋል።

እንደሚታወሰው ኢትዮጵያዊቷን አሰልጣኝ ሰላም ከላይቤሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሦስት አመት ውል ከስምምነት በመድረስ ፊርማዋን ያኖረችው  እንደሆነ  ሲታወቅ ከስምምነቱ ውስጥም  አሰልጣኟ የ17 ዓመት እና የ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖችን መከታተል እንዲሁም የተለያዩ የካፍ ስልጠናዎችን ለአሰልጣኞች እንደ ምትሰጥ በስምምነቱ መካተቱ ይታወሳል።