🔔- ሀጎስ የኢትዮጵያን ሪከርድ ሰብሯል !
በኦስሎ የምሽቱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደናቂ ብቃት አሳይተዋል።
ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ሀጎስ ገብረሕይወት በ5000ሜ. 12፡36.73 በሆነ ሰአት፣በታሪክ ሁለተኛ ፈጣን ሆኖ ሲያሸንፍ በኢትዮጵያ አዲስ ክብረወሰን ሆኖ አጠናቋል።
በ5ሺ ህ ሜትር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 12 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ ይዞት የነበረውን የኢትዮጵያ ክብረወሰን ነው አትሌት ሀጎስ ማሻሻል የቻለው ።
ሌላው ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ 12፡38፡95 በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃን አግኝቷል።