
የ18 አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አይዛክ አለማየሁ ሙሉጌታ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የስዊዲኑ ጁርጋርደን IF ከእንግሊዙ ቼልሲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ለክለቡ ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል ::
በአውሮፓ ኮንፈሬንስ ሊግ የምሽቱ ጨዋታ ቼልሲን ጁርጋርደን 4 ለ 1 አሸንፏል።
በአባቱ የኢትዮጽያው የሆነው አይዛክም እንዲሁም አባቱ ከአገር ቤት የወላይታ ዲቻ የልብ ደጋፊዎች መሆናቸው ተሰምቷል:: የ18 አመቱ አይዛክ ተወልዶ ያደገውም ስዊድን ሲሆን በእናቱ የኤልሳልቫዶር ተወላጅ መሆኑ ታውቌል::