የዛሬው ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጨዋታ ውጤት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እጅ ላይ ነው ለሚለው አሰልጣኙ ምላሽ ሰጥተዋል!
“እንደዚህ አይነት አባባል መድንን አይመለከተውም ቀድሞ ያልተሰራ ነገር ከመድን ጋር ባለው ጨዋታ ሊሆን አይችልም “
– አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛው ሳምንት ሻምፒዮናውን የሚለይበት ተጠባቂ ጨዋታዎች በተመሣሣይ ሰአት ዛሬ ሰኔ 29 በ10: 00 ሰአት ኢትዮጵያ መድንን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እና መቻል ከድሬዳዋ ከተማ በሀዋሳ ሰው ሠራሽ ሜዳ የሚደረጉ ይሆናል .
የቻምፒዮናው ክብር ለማንሳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን በ61 እንዲሁም መቻል በ60 ነጥብ በአንድ ነጥብ በቅርብ ርቀት በመካከቸው በመሆኑ ጨዋታውን እስከመጨረሻው ተጠባቂ አድርጎታል.
የዛሬውን ተጠባቂ ሁለት ጨዋታዎች አስመልክቶ የተለያዩ አሳቦች በማህበራዊ እና ሌሎችም ሜዲያዎች መሰጠታቸው አይቀሬ ነው. በተለይ ለዋንጫ አሸፊነት ተጠባቂው ከሆነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የመርሐግብር ጨዋታውን በሚያደርገው ኢትዮጵያ መድን ላይ የተለያዪ አሰባቦች ተሰጥተዋል..
ከተሰጡ ሐሳቦች መካከል ‘ ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርገው ጨዋታ ውጤት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ / መድን እጅ ላይ ነው የሚል ሲሆን በዚህ እና የዛሬውን ጨዋታ አስመልክተው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለኢትዮ ኪክ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል.
“እንደዚህ አይነት አባባል መድንን አይመለከተውም. እኛ የራሳችን ስራ እንሰራለን ሌሎችም እንዲሁ የራሳቸውን ስራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል.ቀድሞ ያልተሰራ ነገር በመጨረሻ ከመድን ጋር ባለው ጨዋታ ሊሆን አይችልም ” ካሉ በኃላ አሰልጣኙ አያይዠውም
“በዛሬው ጨዋታ በመድን በኩል በሁለተኛው ዙር መድን ያሳየውን መሻሻሉን በዚህ ጨዋታ ላይ ማሳየት እፈልጋለን. ከዚህ በተጨማሪም ለማሊያ መጫወት ማለት ምን ማለት እንደሆነም በዚህ ጨዋታ ማሳየት ስለምንፈልግ ጨዋታውን ለየት ያረገዋል. በአጠቃላይ እኛ ጨዋታውን ለማሸነፍ እንጫወታለን. “በማለት በአጭሩ መልሰዋል.
የዛሬው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ መድን የጨዋታ መርሐ ግብር በሚደረግበት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የዋንጫ አሸናፊው ክለብ የዋንጫ እና የሜዳሊያ ዝግጅቱ የሚደረግበት ሲሆን መቻል ድሬደዋን ቢያሸንፍ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ቢጥል ለዋንጫ ዝግጅቱ መቻል ከሀዋሳ ሰው ሠራሽ ሜዳ ወደዚሁ ስታድየም የሚመጣ ይሆል. በተጨማሪም የቀጥታ ስርጭት ሽፋንም ከዚሁ ሜዳ ላይ የሚደረግ ይሆናል.