ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

⭕የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሚያዝያ 28 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት በመሸናነፍ ቀሪ አንዱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 21 ጎሎች በ17 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 28 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።

በሳምንቱ በሁለት ተጫዋቾች ላይ ተመሳሳይ የየዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ካሌብ አማንክዋህ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) እና አማኑኤል ተርፉ(ቅዱስ ጊዮርጊስ) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።