በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአፍሪካ በምድብ አንድ የተመደበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን November 15 ( ህዳር 5 ቀን ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር በሜዳው ማድረግ የሚገባውን ጨዋታ በሞሮኮ ካዛብላንካ ስታዲየም የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። ይህም ብሔራዊ ቡድኑ የፊፋን መስፈርት ሟሟላት የቻለ ስታዲየም ባለመኖሩ እና የባህር የዳር ስታዲየም በወቅታዊው ሁኔታ ማስተናገድ ባለመቻሉ የሜዳ ጨዋታን ብሔራዊ ቡድኑ እንደተለመደው ሞሮኮ ላይ ያደርጋል ማለት ነው።
በተጨማሪም ቡድኑ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በቀናቶች ልዩነት ከቡርኪናፋሶ ጋር የሚያደርገውን ሌላኛውን የማጣሪያ ጨዋታም በተመሳሳይ የሜዳ ችግር ቡርኪናፋሶም ጨዋታው ሞርኮ ካዛብላንካ እንዲሆን በመወሰኗ ሁለቱም ጨዋታ ሞሮኮ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።
በሌላ በኩል የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ቡድን ቀጣይ አሰልጣኝ እስካሁን በይፋ ማሳወቅ አልቻለም። በፌዴሬሽኑ ከኩል አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ጋር የተስማማሙ ቢሆኑም በሊጉ ውድድር የሚገኘው መድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ለለመልቀቅ የቀረበለትን ጥያቄ እና አሰልጣኙ የሊጉ ውድድር መቋረጥ በኃላ ብሔራዊ ቡድኑን ለአጭር ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ መረከብ በሚለው የጋራ ስምምነት ከመድረሳቸው ውጪ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጉዳይ ፌዴሬሽኑ አሁንም በዝምታ ይዞታል