ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ጎል ለማስቆጠር ፈጣሪ ነው የረዳኝ ፣ፈጣሪን ጠየኩት አደረገልኝ ለዛም ደግሞ ደስ ብሎኛል ” -ተመስገን ብርሃኑ

ተመስገን ብርሃኑ ደሰታውን ሲገልዕ

 በሀዲያ ሆሳዕና በዛሬው ጨዋታ ከተቆጠሩት ሦስት ጎሎች የመጨረሻውን እና የውድድር ዓመቱ 369 የማሳረጊያ ጎል ያስቆጠረው ተመስገን ብርሃኑ ነው። ታዳጊው  ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።

በቅድሚያ እንኳን ደስ ያለህ
” ያው እንኳን አብሮ ደስ አለን። ጎል ለማስቆጠር ፈጣሪ ነው የረዳኝ። ፈጣሪን ጠየኩት አደረገልኝ ለዛም ደግሞ ደስ ብሎኛል “
ጎሉን ካስቆጠርክ በኃላ ማሊያ ለማውለቅም ፈልገህ ነበር ፣ ደስታህ ምን ያህል ነበረ?
“ያው ደስታዬ እስካሁን የለፋንበት ነው። በዛውም የመጨረሻ ጨዋታ ስለሆነ ደስታዪን መግለፅ አልቻልኩም ነበር።ላወልቅም አሰብኩ ከፈጣሪ ጋር እጣላለሁ። በዚች ገና በጅማሬ ላይ ይን ከማደርግ ብዬ ነው የተውኩት። ያው ከዚህም በኃላ ፈጣሪ ይረዳኛል። የተሻለ ሰርቼ አሪፍ ነገር ለማሳየት ነው። አመሠግናለሁ”
ውድድር ዓመቱን የመዝጊያ ጎል አስቆጥራለሁ ብሎ አስቦ ስለማወቁ ?
” አዎ! ማታም ለፈጣሪ ስፀልይ ነበረ ፈጣሪ አሳክቶልኛል። ደስ ብሎኛል። የመጀመሪያ ስለሆነ መነሻ ስለሆነ ብዙም ደስ አላለኝም ። ምክንያቱም ከዚህ የተሻለ ነገር ነው መስራት የምፈልገው ፣ይሄ ገና ጅማሪ ስለሆነ ደስታው ብዙም ነው”
ጎሏን ለአንድ ሰው ስጥ ብትባል ለማን ትሰጣለህ ?
” ጎሉን ለማዘር ብሰጥ ደስ ይለኛል። ማዘር ናት ለዚህ ደረጃ ተጨዋች እንድሆን በሷ ብርታት ነው። እሷ ናት የምትረዳኝ ማቴሪያል፤ ታኬታ ስል ከየትም እሷ ናት የምትሰጠኝ ለማዘር”

One thought on ““ጎል ለማስቆጠር ፈጣሪ ነው የረዳኝ ፣ፈጣሪን ጠየኩት አደረገልኝ ለዛም ደግሞ ደስ ብሎኛል ” -ተመስገን ብርሃኑ

Comments are closed.