የአሜሪካው ሃርትፎርድ አትሌቲክስ የቅዱስ ጊዮርጊሶቹን ጋቶች ፓኖም እና አቤል ያለውን አሜሪካ እንዲቆዮና የአንድ ሰምንት የሙከራ ጊዜ እንዲያደርጉ በሰጠው ዕድል መሠረት ከሰፈረረኞቹ ጋር የኮንትራት ጊዜው የተጠናቀቀው ጋቶች ፓኖም እዛው አሜሪካ በመቅረት ከክለቡ ጋር የአንድ ሳምንት የሙከራ ጊዜ የሚደርግ ይሆናል። የሙከራ ጊዜው ከተሳካ ደግሞ ጋቶች ከዋናው ሊግ ቀጥሎ ለሁለተኛ ዲቪዚዮን ለሚወዳደረው Hartford Athletic ክለብ የመጫወት ዕድል ያገኛል ማለት ነው።
ሌላኛው በHartford Athletic ክለብ የሙከራ ዕድል ያገኘው ተጨዋች አቤል ያለው ሲሆን አቤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር የአንድ ዓመት ኮንትራት ውል በመኖሩ በአሜሪካ ለመቆየት ያደረገው ሙከራ ሊሳካለት ባይችልም፣ ተጨዋቹ አዲስ አበባ ከሚገኘው የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ጋር በመደወል የአሜሪካ ዕድሉን ለማሳካት ጥረት ማድረጉ ታውቋል።
ሌሎቹ በDC United እና በሌላኛው የሁለተኛ ዲቪዝዮን ክለብ የሙከራ ጊዜ ዕድሉን ያገኙት ተጨዋቾች ደግሞ ዘንድሮ በ2015 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ብቃቱን ያሳየውና ከፈረሰኞቹ ጋር የ1 ዓመት ውል ያለው ቢኒያም በላይ፣ ሲሆን የግብፅ ሊግ ረጅም ዓመት የተጫወተውና አሁን ነፃ የሆነው የቡድኑ አምበል ሽመልስ በቀለ ፣ ከፋሲል ከነማ ጋር የአንድ ዓመት ውል ያለው ሱራፌል ዳኛቸው እና ረመዳን የሱፍ በክለቦቹ የተፈለጉ ሲሆን በአሜሪካ የሙከራ ዕድል ለማድረግ ከክለባቸው ጋር ኮንትራት በመኖሩ የሙከራ ጊዜ ማድረግ አልቻሉም።
ለዚህ ደግሞ በዋነኛነት የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኃላፊነት አሜሪካ ያመጣኃችሁ እኔ በመሆኔ እኔው ወደ ሀገር ቤት መመለስ አለብኝ በማለቱ ከክለባቸው ጋር የኮንትራት ያላቸው ተጨዋችች አዲስ አበባ ተመልሰው ከክለባቸው ጋር ተነጋግረው ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ በሚል ተጨዋቹ ከቡድኑ ጋር ወደ ሀገር ቤት ዛሬ ይገባሉ።
Congratulations