ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የዛሬው ሶስት ነጥብ ከኛ በላይ ለድሬዳዋ ደጋፊዎች እና ለድሬ የስፓርት አፍቃሪዎች ይገባቸዋል “–ኢታሙና ኬሙይኔ

ኢታሙና ኬሙይኔ---ድሬዳዋ ከተማ
ኢታሙና ኬሙይኔ—ድሬዳዋ ከተማ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል። የድሬዳዋን ማሸነፊያ ግቦች ሪችሞንድ አዶንጎ ፣ኢታሙና ኬሙይኔ እና ሰዒድ ሀሰን በራሱ ላይ ሲያስቆጥሩ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ሙጂብ ቃሲም አስቆጥሯል። ከጨዋታው በኃላ ኢታሙና ኬሙይኔ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
በቅድሚያ ጎል በማስቆጠሩ እና በጨዋታው በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለህ
” አመሠግናለሁ ።በቅድምያ ለእግዚአብሔር ምስግና አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ ለሻምዮኖቹ ለፋሲል ከነማ ቡድን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም ሪከርድ ለሰበረው አቡበከር ናስር እንኳን ደስ ያለህ ማለት እፈልጋለሁ ፣ በጣም ጥሩ ስኬት ነው ማለት እችላለሁ “
የቋሚ ተሰላፊ በአጋጣሚ ዛሬ በተጎዳው ናንጄቦ ምትክ ማግኘቱ እና ጎል ማስቆጠሩ ዕድለኛ ከመሆኑ አንፃር ሊባል ስለመቻሉ
” እንደዛ ልለው አልችልም ፤ ይሁንና በዛሬው ጨዋታ መጫወት ችያለሁ። በእኔ በኩል ዕድሉን ባገኘው ጊዜ ሁሌም ዝግጁ ነኝ። በዛሬው ጨዋታ መሠለፍ በመቻሌም በጣም ደስታ ነኝ “
ኢታሙና ኬሙይኔ---ድሬዳዋ ከተማ
ዛሬ ያገኙት የሶስት ነጥብ በተመለከተ
”  ውጤቱ ቡድኑን ከጭንቀት አላቆ ደረጀው ላይ ከፍ የሚልበት  ሶስት ነጥብ  ነው። ይሄ  የዛሬው ሶስት ነጥብ ከኛ በላይ ለድሬዳዋ ደጋፊዎች እና ለድሬ የስፓርት አፍቃሪዎች፣ ቤተሰብ በአጠቃላይ ይሄ ድል ለነሱ ነው።  ደስታው ይገባቸዋል። የዛሬዎ ደስታ ቡድኑን ከጭንቀት ተላቆ ወደ ላይ ከፍ የሚልበት በመሆኑ በዛሬው ሶስት ነጥብ በጣም ደስቸኛ ነኝ”
አቡበከረን ናስር ችሎታን በተመለከተ
” ዋው ዋው ዋው…. አቡበከርን በቃላት ለመግለፅ ስለምቸገር ዋው ዋው በሚል ብገለፀየው ይመረጣል። በጣም ድንቅ ተጨዋች ነው። በዚሁ አቋሙ ለቀጣይ ዓመታትም ገና የምናየው ይሆናል እና ድንቅ ተጨዋች ነው።