የባህርዳር ከነማ የፊት መስመር ተጫዋች ዱሬሳ ሹብሳ በፌስቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረዉ መልእክት: መሠረት አድረገን ኢትዮኪክ ተጨዋቿን ያሰፈረው መልዕክና ውሳኔ ትክክል ስለመሆኑ ጠይቀነው ተጨዋቹ ትክክል ነው ብሎናል።
በዚህ መሠረት ዱሬሳ ከክለቡ ጋር በፍቃዱ መለያየቱን አረጋግጦልናል።
የተጨዋቹ መልዕክት
“ለባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ና ሚዲያ
ዛሬ ይህንን ፅሁፍ ስፅፍ ለሁላችሁም በተለይም ለደጋፊዎቹና ለክለቡ የልብ ውዳጆች እንዲሁም የቡድን ጕደኞቼ ማሳውቅ ያለብኝን እውነት ለማሳወቅ ነው::
እኔ ከባህርዳር እግር ኳስ ክለብ ጋር ባልፈው ዓመት ጥሩ ሲዝን ማሳለፍ ችያልሁ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣም ከቡድን አጋሮቼ ጋር በመሆን አቅሜ በፈቀደው ሁሉ የተቻለኝን በማድረግ ቆይቻለሁ ::
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከክለቡ አሰልጣኝ ጋር መግባባት ባለመቻላችን ያለውን ሁኔታ በመገለፅ ለክለቡ ችገሩ እንዲፈታ ካልሆነም ከክለቡ ጋር ያለኝ ውል እንዲቋረጥ በፅሁፍ አመልክቼ ነበር::ነገር ግን ችግሩ ሊፈታ ይቅርና እልክ በሚመስል መልኩ አሰልጣኙ አንተ አታስፈልገኝም በማለት ቃል በቃል ከመናገሩም በላይ ባለፈው ዓመት የሊጉ የመጨረሻ ሳምንታት ጫወታዎች ጀምሮ እንደነበረው ምንም የአካል ብቃት ችግር ሳይኖርብኝ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እንድቀመጥ ሲያደርገኝ ቆይቷል::ይህ ሁኔታ እኔን ሞራል ለማሳጣት ሆን ተብሎ የተደረገና የነገ ሕልሜን ለማጨለም በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ ስለደረሰብኝ::ክለቡም ማመልከቻዬን ተቀብሎ በአካል ከማነጋገር ይልቅ ዝምታን መምረጡ ሰላልተስማማኝ የራሴን ወሳኔ ለመወሰን ተገድጃለሁ::
በነበረኝ የክለቡ ቆይታ ላሳያችሁኝ አክበሮትና ለሰጣችሁኝ ልዩ ፍቅር የባህርዳር እግር ኳስ ደጋፊዎች ምስጋናዬ ከልብ ነው እንዲሁም የቡድን አጋሮቼ ከልቤ እያመሰገንኩ መልካሙን ሁሉ እመኝላችሁአለው::”
ዱሬሳ ሹቢሳ (ዱዱ)