ዜናዎች

የዝውውር መረጃዎች # ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዪም ከበደ እና ኦኪኪ አፎላቢ

አሰልጣኝ ስዪም ከበደ
ለ2014 የወድድር ዘመን የሊጉ ክለቦች ጠንካራ ቡድን ሆነው ለመቅረብ  የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች ይፋዊ ባለሆነ መልኩ የስምምነት ስራዎችን ጀምረዋል።በ2013 የውድድር ዓመት የቤትኪንግ ሻምፒናው ፋሲል ከነማ በቀጣይ ዓመትም ለሚጠበቀው የሀገር ውስጥ እና የአፍሪካ ሻምዮንስ ሊግ ውድድር ጥንካሬውን ለማስጠበቅ እና ቡድኑን የበለጠ ለማጠናከር አዳዲስ ተጨዋቾችን የማግባባትና የውስጥ ለውስጥ ድርድሮች መሰማት ቀጥሏል ።
ዛሬ ከተሰማው የኦኪኪ አፎላቢ መረጃ በፊት ሰሞኑን ይፋ በሆነው ሌላኛው የአሰልጣኞች መረጃ የፋሲል ከነማው ወጤታማ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከፋሲል ከነማ ጋር በቀጣይ ዓመትም የሚያቆያቸውን ውል ለአንድ ዓመት መቀጠላቸው ተረጋግጧል ።
ከዚህ በተጨማሪም አሰልጣኝ ስዪም ከበደ ቡድናቸው ለሚጠብቀው የአፍሪካ የክለቦች ሻምዮንስ ሊግ ጨዋታዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም መጀመራቸው ታውቋል።
ሌላው የሲዳማ ቡናው ኦኪኪ አፎላቢ እና ፋሲል ከነማ በተሰማው የዛሬው መረጃ ሁለቱ አካላት ሙሉ ለሙሉ መስማማታቸው ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ተሰምቷል።
በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ከጠንካራ ክለቦች ጋር ጠንካራ ጨዋታ የሚጠብቃቸው ፋሲል ከነማዎች ከሲዳማ ቡና ኦኪኪ አፎላቢ በቅርብ ቀናት ይፋዊ በሆነ መልኩ ስምምነት እንደሚያፀድቁት ይጠበቃል።
ጉዳዩን አሰመልክቶ ኢትዮኪክ ናይጄሪያዊውን ኦኪኪ አፎላቢ ጠይቀነው ተጨዋቹ ሲመልስ ” አሁን ባለው ሁኔታ በትክክል ያለውን ነገር ለመናገር እርግጠኛ አይደለሁም ፤ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ማለት የምችለው ለሁሉንም ነገር እግዚአብሔር ያውቃል ብቻ ነው ” በማለት በአጭሩ ተጨዋቹ  ምላሽ ሰጥቷል።