ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የዛሬው ጨዋታ በጣሞ አስፈላጊ ነበረ። ሶስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት ነበር የመጣነው ግን አልተሳካም ፣ ሃዋሳ ላይ ተሻሽለን እንቀርባለን”.- ረመዳን የሱፍ

በወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል የ10ሺህ ብር ተሸላሚ የነበረውና በዛሬው ጨዋታ ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ረመዳን የሱፍ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ዛሬ ስላስቆጠረው ጎል
” ቡድናችን እዚህ ከመጣን በኋላ ምንም ውጤት አልያዝንም። እዚህ ድሬዳዋ ላይ የመጨረሻ ጨዋታችን ነው ። ሶስት ነጥብ ይዘን ለመውጣት ነበር። ወሳኝ ጎል በማግባቴ በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ። ቡድንኔም ከጭንቀት አወጣለሁ ብዬ ነበር ግን ባለቀ ሰዓት የተቆጠረብን ጎል ዋጋ አስከፍሎናል”
አጠቃላይ የዛሬው ጨዋታ
” የመጀመሪያው 45 ጥሩ ተንቀሳቅሰን ነበር ። ጎሉን ካገባን በኃላ በጣም ወደ ኃላ አፈግፍገን የመጫወት ነገር ነበረ። ያ ደግሞ ጫና ራሳችን ላይ አምጥቶብናል። እኛ በሸሸን ቁጥር እነሱ ተጭነውን መጥተው ባለቀ ሰዓት አቻ ወጣን”
የዛሬው ውጤት ምን ያህል አስፈላጊ ነበረ
“የዛሬው ጨዋታ በጣሞ አስፈላጊ ነበረ። ሶስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት በሙሉ ልባችን ነበር የመጣነው። ጥረትም አድርገን ግን አልተሳካም። ሃዋሳ ላይ ያለውን ጨዋታ በጣም ተሻሽለን እንቀርባለን።
በደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተብሎ በሜዳ ውስጥ በጨዋታው ላይ የሚሰጠው ተፅዕኖ
“በጣም ደስ ቤሎኛል። እኔ አልጠበኩትም ነበር። ኮከብ ተብዬ በመመረጤ በጣም ደስ ብሎኛል። በዚህ አጋጣሚ ደጋፊዎችን አመሠግናለሁ።
ጎሏ ለማን ትሁን ?
* ለደጋፊዎችና ለእናቴ “