የሴራሊዮን 17 በውጭ ሀገር የሚጫወቱት ከነገ ጀምሮ ቡድኑን ይቀላቀላሉ
በ2026 የፊፋ የአለም ዋንጫ የአፍሪካ ምድብ ማጣሪያ ከሴራሊዮንና ከቡሪኪናፋሶ ጋር በሞሮኮ አል ጀዲዳ ከተማ -ኤል አብዲ ስታዲየም የሚያደረገው 23 ተጨዋቾች የያዘው ኢትዮጵያ የልኡካን ቡድኑ ሞሮኮ ደርሷል። ቡድኑ በካዛብላንካ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ማረፊያውን አድርጓል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ሴራሊዮን ሰባት የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች እና አስር ከቡድኑ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው የልዑካን አባላት ሞሮኮ መድረሳቸውን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ህዳር-5 /2016 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን “ሊዮን ስታርስ” ዝግጅታቸውን ቀደም ብለው ነበር የጀመሩት። ከሦሰት ሳምንት የሴራሊዮን አሰልጣኝ አሚዱ ከሪም የመረጧቸውን 35 ተጨዋቾች ይዘው ሞሮኮ በመገኘት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ከቤኒን እና ከሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርገው አቋሟቸውን በመጠኑም ፈትሸው ነበር የተመለሱት።
የሴራሊዮን አሰልጣኝ አሚዱ ከሪም በቀጣይ ከኢትዮዽያ እና ከግብፅ ጋር ለሚኖራቸው ጨዋታ 24 ተጨዋቾችን ትላንት ይፋ አድርገዋል። አሰልጣኙ በማጣሪያው ከምድቡ የተሻለ ሆኖ ለማለፍ በብሔራዊ ቡድኑ ወስጥ በእንግሊዙ ቼልተንሃም ታውን የሚጫወተውን ፕሮፌሽናል እና ልምድ ያለው ኩርቲስ ዴቪስ ጨምሮ በሌሎች ሊጎች የሚጫወቱ 17 ተጨዋቾችን አካተዋል።
በዚህ መሠረት የሴራሊዮን የብሄራዊ ሰባት የሀገር ውስጥ ተጨዋቾች ሞሮኮ የደረሱ ሲሆን ቀሪዎቹ 17 በውጭ በሌሎች ሊጎች የሚጫወቱት ተጨዋቾች ከነገ ጀምሮ ቡድኑን ይቀላቀላሉ።