አፍሪካ ዜናዎች

የዋልያዎቹ አለቃና እና አምበል ነገ ከአልጄሪያ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል!

” ጨዋታውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁ ነን “
-አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
“በአካል ብቃቱም ሆነ በአእምሮ ረገድ ተዘጋጅተናል “
-አምበሉ መስዑድ መሀመድ
👇
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከአልጄርያ አቻው ጋር ካለበት ጨዋታ አስቀድሞ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ መስዑድ መሀመድ የቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ምን ተባለ ?
አስቀድመው ስለነገው ጨዋታ የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ” ተጫዋቾቻችን በቶሎ እንዲያገግሙ በማድረግ ለነገው ጨዋታ ዝግጅታችንን ቀጥለናል።
ለዝግጅት ያለው ቀን አነስተኛ በመሆኑ በአዕምሮ እና በአካል ብቃቱ ረገድ ተጫዋቾቻችን ጠንካራ እንዲሆን እየሰራን ነው ፣ ወንድማገኝ ሀይሉ ባጋጠመው ጉዳት ከነገው ጨዋታ ውጪ ነው ከእሱ ውጪ ያሉት ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
የምንጫወተው ከአዘጋጅ ሀገር ጋር መሆኑ ይታወቃል የሚጫወቱት በደጋፊዎቻቸው ፊት ነው በከፍተኛ የራስ መተማመን ውስጥ ሆነን ጨዋታውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁ ነን ” ሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናግረዋል።
የቡድኑ አምበል መስዑድ መሀመድ በበኩሉ ” ከመጀመሪያው ጨዋታ ” ሪከቨር ” በማድረግ ለነገው ጨዋታ እየተዘጋጀን እንገኛለን ከመጀመሪያው ጨዋታ ፍፁም የተለየ መርሐ ግብር ነው ፣ በአካል ብቃቱም ሆነ በአእምሮ ረገድ ተዘጋጅተናል ” ሲል ተደምጧል።
በተያያዘ ዜና በነገው ጨዋታ ላይ አጥቂ ወንድማገኝ ኃይሉ በጉዳት እንደማይሰለፍ ታውቋል ።
@ቲክቫህ ስፖርት
መረጃ
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-
24,019
People reached
1,114
Engagements

+1.5x higher

Distribution score
Boost post
461