ዜናዎች

የወላይታ ድቻ ተጨዋቾቹ ከኮቪድ ነፃ ናቹ ሲባሉ አሰልጣኝ ዘላለም በዛሬው ጨዋታ አይኖርም !

በቤትኪንግ የ19ኛው ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻ አንድም ተቀያሪ ተጨዋች ሳይኖረው በ11 ተጨዋቾች ብቻ ሃዋሳ ከተማ ገጥሞ ጨዋታን በ3 ለ 2 ተሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወሳል። ከቀናት በፊት ተቀያሪ ተጨዋቾች ያልነበረው እና  በአጥቂ ቦታ ላይ ግብ ጠባቂዎቹ መክብብ እና አብነት   ያሰለፈው ወላይታ ድቻ በዛሬው የምርመራ ውጤት ደግሞ ከእዮብ አለማየሁ ውጪ ሁሉም የወላይታ ዲቻ ተጫዋቾች ከኮቪድ ነፃ ናችሁ ሲባሉ አሰልጣኝ ለዘላለም ሽፈራው የኮቪድ  አለብህ ተብለዋል።
ዛሬ ረፋድ የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከስፖርት ዞን አዘጋጅ ሰኢድ ኪያር ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የኮቪድ ምርመራ ጋር እያጋጠማቸው ያለውን ከፍተኛ ችግርም በስፋት አንስተውም አሰልጣኙ ተናግረዋል። በተለይም ኮቪድ ምርመራው ውጤት ከሁለት የጤና ተቋማት የተለያዩ መሆን በክለቦች ላይ ትልቅ ተፅኖ እንዳለው ገልጿል። እንደምሳሌም በቡድናቸው ባጋጣሚ ያልተመረመሩ ተጨዋቾች ጨምሮ አለማያ ዩኒቨርስቲ ኮቪድ አለባችሁ እንደተባሉ ተናግሯል። አሰልጣኝ ዘላለም እንዳለው  አወዳዳሪው አካል ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግም አሳስቧል።
ወላይታ ድቻ ዛሬ ከሰበታ ከተማ በሚያደርገው ጨዋታ ዋና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በጨዋታ ሜዳ የማይገኝ ሲሆን በሜዳ ላይ ቡድኑን ይዞ የሚገባው ምክትል አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙ እንደሚሆን ይጠበቃል።