የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ዘጠኝ ቀናት ብቻ ሲቀረው የውድድሩ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አስመልክቶ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች ከጨዋታው መጀመር በፊት ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። በተለይም ደግሞ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በተሳታፊ ሀገራት ላይ ሊደርስ የሚችለው የኮቪድ ጫና ሌላኛው ስጋት ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ነው።
ከውድድሩ መጀመር በፊት ባለፈው እሁድ ከሀያ አራቱ ተሳታፊ ሀገራት ቀዳሚው ሆኗል ያውንዴ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አና ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ 1 የምትገኘው አዘጋጇ ካሜሩን እንዲሁም በዚሁ ምድብ የምትገኘውኬፕቨርድ ጥቂት ተጨዋቾቻቸው በኮቪድ ወረርሽኝ መያዛቸውን የካሜሩን መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃውን ይፋ ባያደረግም በትላንትናው ዕለት በዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ 4 ወሳኝ የሚባሉ ተጨዋቾች የኮቪድ ኬዝ እንደተገኘባቸው ታውቋል።ይሁንና ፌዴሬሽኑ መረጃውን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል
በአንፃሩ ከካሜሩን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አራት ተጫዋቾች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የካሜሩን ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። እንደ መረጃው በኮቪድ የተያዙት ከተረጋገጠ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በልምምድ ቦታ ረቡዕ ከሰአት በኋላ አለመገኘኘታቸውን ዘግቧል።
በካሜሩን ብሔራዊ ቡድን በኮቪድ የተያዙት አራት ተጨዋቾች ፒየር ማሎንግ፣ ኢፋላ ኮንጉፕ፣ ሚሸል ንጋድ እና ክርስቲያን ባሶንግ ናቸው። በተመሣሣይ በዚሁ በምድብ አንድ የምትገኘው ከኬፕቨርድ ብሔራዊ ቡድን ተከላካዩ ያኒክ ስኮፒራ በኮቪድ መያዙ ተዘግቧል ።
በዋልያዎቹ በኩል አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከተመረጡት 25 ተጨዋቾች መሀል አሁን ላይ 4 ወሳኝ ተጨዋቾች በኮቪድ መያዝ የአሰልጣኙን ቅደመ አሳብ ሊያስለውጥ እንደሚችል ተናግረዋል። ከዚህ አንፃር ቀድሞ ካሜሩን የደረሰው የኢትያዽያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ኮቪድ የቡድኑ አቋም ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ይገመታል።