ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የእኔ ጊዜ ይመጣል በሚል ጠብቄ ነበር ፤ አሁን የኔ ጊዜ ነው ማለት እችላለሁ ” አቡበከር ኑሪ

የ18ኛው ሳምንት የዛሬው የምሽቱ የሃዋሳ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር  ጨዋታ  በ1ለ1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው ላይ ከታዩ የሁለቱ ቡድኖች የመሸናነፍ እንቅስቃዎች በተጨማሪ በጅማ አባጅፋር በኩል ወጣቱ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በርካታ ዒላማቸውን ወደ ጎል የነበሩ ኳሶችን በግሩም ብቃት ተቆጣጥሮ ጎለ ከመሆን በማዳን የጨዋታው ትኩረት ያገኘ ተጨዋች ነበር ።ከጨዋታው በኃላ አቡበከር ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ለበርካታ ጊዜያት ጅማአባጅፋር በውጭ ተጨዋቾች ነበር ፤ ነገር ግን ይህን ዕድል ጠብቀኸዋል ?
“አይ መጀመሪያም ዕድሉን አግኝቼ ነበር ፤ ነገር ግን እኔ አልተጠቀምኩበትም ። በቀይካር ወጣሁኝ በመጀመሪያው ጨዋታ ። የበረኛ አሰልጣኛችን ደግሞ ጎበዝ ስለሆነ ከእሱ ጋር እየሰራን የእኔ ጊዜ ይመጣል በሚል ጠብቄ ነበር መጥቶል ፤ አሁን የኔ ጊዜ ነው ማለት እችላለሁ “
የኳሰ ስርጭትህ ጥሩ ነበር ፣ወደ ሰባት የሚደርሱ ጎል የሚሆኑ ኳሶችን አድነሃል። ተከላካይ ክፍሉ የተጋለጠ ነበር ማለት ትችላለህ ?
” ትንሽ ተጋልጦ ነበር። እኛ ኳስ ይዘን ለመጫወት ነበር ያሰብነው ። ያው ትንሽ እነሱም እየተጫኑን ነበር ። ለመቋቋም ሞክረናል። ተከላካዮቹ ባይኖሩ ብዙ ጎል ይቆጠርብን ነበር። እነሱም አሪፍ ነበሩ”
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም እየጠራህ በሶስት ደቂቃ ልዩነት ነው ጎሉ የተቆጠረው ምን ነበር መልዕክቱ ?
” ያው አሰልጣኛችን እንጫወት ነው የሚለው ሁሌም። እኛ ጫና ውስጥ ስላለን ። በዛ ላይ ነጥቡን ከነሱ በላይ ለእኛ ስለሚጠቅም እንፈልገው ነበር። አንድ እኩል መሆንም ከመሸነፍ ይሻላል’
ከካዝናውስጥ የገባ ሶስት ነጥብ ነው የወጣው ?
” አዎ በትክከል። ከዚህ በፊትም በመጨረሻ ሶስት ደቂቃዎች ጎል ገብቶብናል። ያው ለቀጣይ ጨዋታ ተዘጋጅተን አሪፍ እንሆናለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ”