ዜናዎች

የኢትዮጵያ እና የጋናን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታወቁ !

 የኳታር 2022 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሁለት ሳምንት በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻቸው ጋር በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኦርላንዶ ስታዲየም የሚያደርጉትን የማጣሪያ ጨዋታ ካሜሮናዊው ንጉዋ ብሌዝ ዩቨን በመሃል ዳኝነት እንዲመሩት ተሹመዋል። በተጨማሪም ካሜሮናዊያኑ ነፊው ኑሁጓዌ እና ማኑዬ ሜፕል በረዳት ዳኝነት ቢቶ ጄኑዎት ደግሞ አራተኛ ዳኛ ሆነዋል። ታንዛኒያዊው አብዲ ሱኡድ የዳኞቹ ታዛቢ እና ኤርትራዊው ጉሁሽ ገብረመህድን የጨዋታው ኮሚሽነር መሆናቸው ተገልጿል።