አፍሪካ ዜናዎች

# የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ወደ አገሩ ዛሬ ለመመለስ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል!

#ከተሳካ ምናልባት ነገ ይደርሳሉ!
በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ከጥር 5/2015 ጀምሮ እስከ ጥር 27/2015 ድረስ በሚቆየው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ከምድቡ ማለፍ ሳይችል በጊዜ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ወደ ሀገሩ ለመመለስ ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል።
በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ላይ ከአንድ ጎል በላይ ማስቆጠር ሳይችል ውድድሩ ላይ በሶስት ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት በምድብ አንድ አራተኛ ደረጃን ይዞ ከውድድሩ የተሰናበተው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን አጠቃላይ የልኡካን ቡድኑ ወደ ሸገር ዛሬ የታሰበው በራራ ትኬት በመጥፋቱ እዛው አልጄሪያ ከአናባ ወደ አልጀርስ ተጉዘው እንዲቆዩ ሆናል።
ለብሔራዊ ቡድኑ ከመነሻው የደርሶ መልስ ትኬት የተቆረጠለት ቢሆንም ቡድኑ በቻን ውድድር የታሰበውን ያህል ብዙ እርምጃዎች ባለመጓዙ ባለቻሉ የመመለሻው ቀን ሊለውጥ ችሏል።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነገ የበሪራ ትኬት የሚገኝ ከሆነ ብሔራዊ ቡድኑ ከአልጀርስ ግብፅ አድርጎ ሸገር ማክሰኞ ሌሊት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ፎቶ 📸ቲክቫህ
መረጃ
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-