ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና ለኮንፌዴሬሽንና ለቀጣይ ዓመት ዝግጅት ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል !

ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እና ለ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዝግጅት እንዲረው የኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ አቅንቷል፡፡ ለአንድ ወር በቢሾፍቱ ከተማ በሚያደርገው ቆይታ ልምምዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሜዳ አድርጎ ማረፊያውን በኪሎሌ ሆቴል እንደሚያደርግ የክለቡ መረጃ ያመለክታል።
በቡድኑ የአሰልጣኞች ስታፉ እንዲሁም ከወጣት ቡድኑ እና ዋናው ቡድን 35 ተጫዋቾች በዝግጅቱ መካተታቸው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ መረጃ ያመላክታል።