ዜናዎች

የኢትዮዽያው የሴካፋ ሻምፒዮና የምድብ ድልድል ቀን ሲታውቅ – ሩዋንዳ ቡድኗን ማሳወቅ ተሰኗቷል !

የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እየተዘጋጀ ይገኛል። 
በአንጻሩ የሴካፋ ዋና ፀሐፊ አኡካ ጋቾዎ ዛሬ እንዳሰታወቁት ከሩዋንዳ በስተቀር ሁሉም አገሮች መመዝገባቸውን  ጠቁመው የቡድኖቹ የዕጣ አወጣጥም  የፊታችትን አርብ ሰኔ 18 (June 25 ) ቀን  በቅጥታ (Zoom)  እንደሚደርግ ተናግረዋል   ።
በአሁኑ ሰአት ሩዋንዳ ከ23 አመት በታች  ቡድኗን  ይፋ ለማድረግ ተቸግራለች። እንደሚታወቀው የሴካፋ ከ23 አመት በታች ውድድር በዚህ ዓመት የታቀደ እና ከ23 ዓመት በታች ውድድሩ ያልተለመደ በመሆኑ ሩዋንዳ ቡድኗን ማሳወቅ ከብዷቷል።
ለምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 በታች ውድድር ቡድናቸውን   ያሳወቁ እና የተመዘገቡ ሀገሮች ዩጋንዳ ፣ ቡሩንዲ ፣ ውድድሩን የምታስተናግደው ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያ ፣ ጅቡቲ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዛንዚባር ፣ ኬንያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ደግሞ ተጋባዥ ሀገር በመሆን ሻምፒዮናው ላይ ትካፈላለች።