አፍሪካ ዜናዎች

– የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ለፋሲል ከነማ እና ለኢትዮጵያ ቡና የሰጠው ቀነ ገደብ እሁድ ይጠናቀቃል !

የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል (ካፍ) እ.ኤ.አ በ2021/2022 በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፉት ክለቦች ላይ ተጨዋቾቻቸውን አስመልክቶ የሰጠው ቀነ ገደብ የአምስት ቀናት የጊዜ ገደብ ብቻ ቀርቶቷል። በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮናው ፋሲል ከነማ  እና የ2013 ዓ.ም በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ኢትዮዽያ ቡና በአፍሪካ መድረክ የሚወክሉት እንደሆነ ይታወቃል።
በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፉት ፋሲል ከነማና ኢትዮዽያ ቡና አሁን ካፍ በሰጠው የአምስት ቀናት ቀነ ገደብ ውስጥ አዲስ ፈራሚ የተጫዋቾቻቸውን ጨምሮ ሙሉ የቡድናቸውን ስም ዝርዝር እንዲያስመዘግቡ  የፊታችን እሁድ ጁላይ 15 ድረስ ቀነ ገደብ ትሰጥቷቸዋል።
 በአፍሪካ መድረክ ለሚወክሉት ለፋሲል ከነማ፣ ኢትዮዽያ ቡና እንዲሁም ንግድ ባንክ  ይኸው ካፍ የሰጠውን ቀነ ቀደብ ምክን ያት በማደረግ  ይፋዊ የዝውውር ሂደታቸውን  ቀደም ብለው ሃምሌ 1/2013 ከመከፈቱ በፊት  የተጫዋቾቻቸውን ዝውውር እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል እንደነበር ይታወሳል።
ፋሲል ከነማ
ፋሲል ከነማና ኢትዮዽያ ቡናም ተጨዋቾችን ሲያስፈረሙ ቆይተው  ላለባቸው የአፍሪካ የክለቦች የቅደመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅትም ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ላለበት የኮንፌዴሬሽን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን ከቀናት በፊት ወደ  ቢሾፍቱ በማምራት  ቡድኑ ለአንድ ወር በቢሾፍቱ ከተማ በሚያደርገው ቆይታ ልምምዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሜዳ አድርጎ ማረፊያውን በኪሎሌ ሆቴል እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተመሣሣይ የ2013 ሻምፒዮናው ፋሲል ከነማ ላለበት የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ዝግጅት ቡድኑ በባህር ዳር አዲስ አምባ ሆቴል መቀመጫውን በማድረግ ዝግጅቱን ጀምሯል።  ካፍ በሰጣቸው ቀነ ገደብ መሠረትም የኢትዮጵያ ተወካይ ክለቦች የተጨዋቾቻቸውን ዝርዝር ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ቡና