ዜናዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ለዋልያዎች 5.6 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽልማት አበረክቷል !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ33ኛ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጲያ ብሔራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን 5.6 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን በአንድነት ተደምሮ ላስመዘገበው ውጤት እጅግ የላቀ ክብርና አድናቆት እንዳለው ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለጹ።
የቀጣዩ አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ በወጣትነት እድሜ ታሪክ ሰርቶ ማለፍ በምኞት የማያገኙት፣ ይልቁንም በትጋት በመስራት የሚጎናጸፉት ክብር ነውና በጥረታችሁ ታሪክ ለማስመዝገብ በመብቃታቹህ፤ ለሃገራችሁ የተለየ የመነቃቃት ስሜት ፈጥራችኃል ብለዋል ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ።
በእግር ኳስ በግል የሚመዘገብ ውጤት የለም ያሉት ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ውጤት የሚመጣው ሜዳ ላይ በሚጫወቱት ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን፣ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተጠባባቂዎች፣ ወጌሻዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ አማካሪዎች፣ ደጋፊዎች … ወዘተ በአንድነት ተጋምደው እንደ አንድ ሆነው ሲሰሩ ብቻ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ብሄራዊ ቡድኑን እና አጠቃላይ ለስፖርቱ እድገት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ለ33ኛ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጸያ ብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎች)5.6 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ ሽለማት የተበረከተ መሆኑን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኘነት መረጃ ያመለክታል ።
በዚሁ መሠረት ፦
ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለእያንዳንዳቸው 40,000
ለፕሬዝዳንቱ ኢሳያስ ጅራ 90,000
ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 200,000
ቡድን መሪ 150,000
ግብጠባቂ አሰልጣኝ 150,000
ምክትል አሰልጣኞች 150,00
ተጠባባቂ ተጫዋቾች 100,000
ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች 150,000 ማበረታቻ እንደተደረገላቸው ታውቋል ።