62 ሺህ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም አለው የተባለለት እና ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የ2ኛው ምዕራፍ ግንባታ ጅማሮ በ900 ቀናት ውስጥ ከ5 ነጥብ 57 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ አስመልክቶ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ሌሎች እንግዶች ዛሬ ሂደቱን ተዘዋውረው ጎብኘተዋል ።
በባህርዳር ዓለም አቀፉ ስታዲየም ዕገዳ ምክንያት ደረጃውን የጠበቀ ምንም ኢንተርናሽናል ስታዲየም የሌላት ኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከጋና አቻው ጋር የሚኖረውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል።
62,000 ተመልካቾችን የሚያስተናግደው እና 8 ቢሊዬን ብር ወጪ የሚደረግበት የአደይ አበባ ብሔራዊ ስቴዲየም በቻይና የኮንስትራክሽን ኩባንያ እና በኢትዮጵያዊዉ ኤም ኤች ኢንጂነሪንግ አማካሪነት ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።