ዜናዎች

#የአቃቂ ስታድየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሆኖ እየተገነባ ይገኛል ሲሉ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አስታወቁ

 

 

 

 

የአቃቂ ዓለም አቀፍ ስታድየም ግንባታ ያለበትን ደረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ጉብኝት አደረጉ።

በጉብኝቱ ወቅት የግንባታው ሒደት ያለበት ደረጃ ፣ ሊስተካከሉ በሚገባቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከስታዲየሙ ተቋረጭ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን አቶ ኢሳያስ ጅራ በስፍራው ለተገጙ የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት አስተያየት የስታዲየሙ የግንባታ ሂደት ተስፋን የሚያጭር መሆኑን ተናግረዋል።

” እንደሚታወቀው ይህ ስታዲየም ሲጀመር ዞናል ስታዲየም ነበር። አሁን ላይ የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሆኖ በጥሩ ሁኔታ እየተገነባ ይገኛል። በተመለከትኩት ነገር ደስተኛ ነኝ ፤ መስተካከል የሚገባቸው ነገሮችም ስላሉ እኛም ባለሙያ ይዘን መጥተን ምልከታ አድርገናል። ከተማ አስተዳደሩ ግንባታውን በጥሩ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ነው ፥ እኛም ተከታትለን ከዳር ለማድረስ ቁርጠኛ ነን።

 

” ሌሎች ላይ ያልተመለከትናቸው ጥሩ ጥሩ ነገሮች አይተናል። መስተካከል የሚገባቸውንም በምልከታችን ወቅት አይተን ምክረ ሀሳብ ሰጥተናል። ስታዲየም ተሰርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ማስተካከያ እንዲደረግ ከማድረግ ይልቅ ከወዲሁ ማስተካከያ እየተደረገበት እንዲጠናቀቅ ነው እየሰራን ያለነው። ካየሁት ነገር ተነስቼ የመመለስ ተስፋ አለው ብዬ አስባለሁ ፤ ባህርዳር ስታዲየም ጥሩ ማስተካከያ እየተደረገለት ነው። ይሄም ከጅምሩ ማስተካካያ እያደረግንበት ከሰራን ተስፋ የሚያጭር ነው። ስታዲየሙ ድምፁን አጥፍቶ ብዙ ስራዎች የተሰሩበት ነው። ከዚህ በኋላ የሚቀሩትም ብዙ አይደሉም። የማጠናቀቂያ ስራዎች እንዳሉ ሆነው ዋናው የመጫወቻ ሜዳው ጉዳይ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ክትትል እናደርጋለን።

” ከተማ አስተዳደሩን ማገዝ ሳይሆን አብረን መስራት ነው ያለብን። በርካታ ጉዳዮች ያካተተ የስታዲየም ደረጃ መመርያ ይዘን እንከታተላለን። ከሀገር ውጪ መጫወታችን ህዝብ እና ሀገርን እየጎዳ ነው። ፌዴሬሽናችንን በፋይናንስ ፣ ቡድናችንም የአየር ንብረት እና የደጋፊ አድቫንቴጅም አጥቷል። ይህን ለመቅረፍ ማገዝ ሳይሆን ዋና ስራችን አድርገን ነው የምንንቀሳቀሰው።” ብለዋል።

 

 

 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው ስታዲየሙ የካፍ እና ፊፋ መስፈርትን ባሟላ ደረጃ ግንባታው እየተፋጠነ እንደሚገኝና በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ግንባታው ሲጀመር በዞናል ስታድየም ስታዳርድ የተጀመረ ቢሆንም የዲዛይን ለውጥ በማድረግ ወደ ኢንተርናሽናል ስታድየም እንዲያድ መደረጉን እና ግንባታው ሲጠናቀቅ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ችግር የሚቀርፍ ይሆናል ብለዋል። በግንባታው ወቅት መካተት ያለባቸው ጉዳዮች እንዲካተቱ እንዲሁም ግንባታው ያለበትን ደረጃ የሚመለከታቸው አካላት እንዲመለከቱት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

@EFF

ሊንኮቻችን
በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick

🔛ድረ ገጻችንን :-

Home page