ዜናዎች

የአለልኝ አዘነን 23 ቁጥር ማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ ክለቡ ወሰነ !

በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ አስታወቀ።
የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ ስፍራው በመገኘት ገልፀዋል።
በዚህም አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰው የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብሰው ሆኖ በክብር እንዲቀመጥ የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ወስኗል።