የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውጥረት ተካርሮ መቀጠሉን መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ዛሬ በኔክሰስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ያረጋገጠም ሆኗል።በተለየም ፍጥጫው በፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እና በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኦሎምፒክ ኮሜቴ ፕሬዝዳንት መካከል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንደሚታወሰው የኦሎምፒክ ውድድሮች በመጡ ቁጥር ተመሳሳይ ውጥረቶች ከዚህ ቀደም የተለመዱ ናቸው። ዘንድሮም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ኦሎምፒክ ኮሚቴ ታላቅ ፍጥጫ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ የቶኪዮ ኦሎፒክ ዝግጅትም እክል እየገጠመው ሆኗል። ይህን ውጥረት አስመልክቶም ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አትሌት ገዛኸኝ አበራ እንዲሁም ከሌሎች ባለሙያዎች ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ ሃሳቦች የተሰጡ ሲሆን የቶኪዮ ኦሎፒክ ዝግጅት እክል የገጠመው መሆኑ ተረጋግጧል።ዛሬ በመግለጫው ላይ ከተነሱ ሃሳቦች በከፊል” ኦሊምፒክ ኮሚቴው ሁልጊዜ አምባገነን በመሆኑ ምክንያት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትም እክል እየገጠመው ነውና ምን እናድርግ?””ለኦሊምክ ዝግጅት አትሌቶች ሆቴል ሲገቡ እንክብካቤና ክትትል ማድረግ የሚገባው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ነው። ነገር ግን አትሌቶች ሌላው ቀርቶ ውሃ እንኳን በአግባቡ እያገኙ አይደለም::”” ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለአትሌቶችና ለአሰልጣኞች መክፈል የነበረበትን ላብ መተኪያ ክፍያ ባለመክፈሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለመክፈል ተገዷል”