# ኑሮን ለማሸነፍ የንግድና ራይድ ሹፍርና የጀመሩ ተጨዋቾች መኖራቸው ተሰምቷል!
የኢትዮዽያ ክለቦች የተጨዋቾቾን ደሞዝ ያለመክፈል ጉዳይ ከዓመት ዓመት በስፋት ቀጥሎ ዘንድሮም በይፋ በቀጥታ የ DSTV ስርጭት የዋልያዎቹ የቀድሞ ተጨዋች እና የወልቂጤ ከተማ አምበል ጌታነህ ከበደ እስከመናገር ደርሷል።
በርግጥ በሊጉ ከሚገኙት 16 ክለቦች መካከል የወልቂጤ ከተማ እና የለገጣፎ ተጨዋቾች አሳዛኝ ችግር በይፋ ቢናገሩም አሁን በዋናው ሊግ ከሚወዳደሩ ከተወሰኑ ክለቦች በስተቀር አብዛኞቹ ክለቦች የተጨዋቾች ደሞዝ በአግባቡ እንደማይከፍሉ ይታወቃል። ክለቦች በሕጋዊ መንገድ ያስፈረሟቸውን ተጨዋቾች በውል ስምምነታቸው መሠረት የወርሃዊ ክፍያ መፈፀም ግዴታቸው ነው።
ይሁንና ጥቂቶቹ ክለቦች የደመወዝ መክፈል ብቻ ሳይሆን ክለቦቹ የሚከታላቸው አካል በተለየም ሲያሸንፉና ሲሸነፉ የሚከታላቸው እንደሌለ የወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ በቅርቡ የተናገረው አንድ ማስረጃ ይሆናል ጌታነህ እንዳለው ” ዞር ብሎ የሚያየን የለም። በቃ በራሳችን ነው የምንጥረው ” ማለቱ ይታወሳል።
እንደሚታወቀው አብዛኞቹ ክለቦች በክልሎች / ከተማ ከመተዳደራቸው አንፃር የዓመት በጀት ፋይናንስ በሚገኘው ገንዘብ የዓመቱ መጀመሪያ በከፍተኛ የፊርማ ወጪ በአንድና በሁለት ተጨዋቾች ገንዘቡን ከማድረግ በተጨማሪም ክለቦቹ ከተወሰነ ወራቶች በኃላ የፋይናንስ ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ የተጨዋቾች ጩኸት ሰሚ አልባ መሆናቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ ጎን ለጎን ክለቦቹ የፋይናንስ አቅማቸውን በተለያዩ መልኩ ለማጠናከር ብሎም የገቢና የስፖንሰርሺፕ ጥቅሞች ለመጠቀም የሚሰሩት ጥቂት ክለቦች እንጂ ብዙዎቹ የፋይናንስ ችግሩ ቀጥኛ ተጎጂ ናቸው።
በተቃራኒው ታዲያ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች በእግርኳስ ተጨዋችነት በሚገኙት ገቢ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት እና የሚረዱ ከመሆኑ አንፃሩ ከ 6 ወራት እና 8 ለወራቶች ደሞዝ አለመከፈላቸው በተጨዋቾቹ ብቻ በዙሪያቸው ያሉ የቤተሰብ አባልን ምግብ እያሳዪ በረሃብ እንደመቅጣት ነው።
በሌላ በኩል ይህን የፋይናንስ ችግር ተከትሎ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አንዳንድ ተጨዋቾች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የፋይናንስ ችግሩን ለመፍታት እየጣሩ መሆናቸው ሲሰማ አንዳንድ ተጨዋቾች የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሁም ራይድ ሹፍርናም የታዮ ተጨዋቾች መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል።