ዜናዎች

የብሔራዊ ብድን 3 ተጨዋቾች ከቡድኑ ወጪ ሲሆኑ አሰልጣኝ ውበቱ ተጨማሪ እንደማያካትቱ ተገምቷል !

  የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ ለ35 ተጫዋቾችም ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

 

ከ35 ተጨዋቾች የጅማአባጅፋሩ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ፣ የአዳማ ከተማው አብዲሳ ጀማል እና የወልቂጤ ከተማው ረመዳን የሱፍ ከብሔራዊ ቡድኑ ውጪ መሆናቸው ይፋ ሆኗል።ተጨዋቾች ከቡድኑ የተሰናበቱት ቡድኖቻቸው በሊጉ ለመቆየት በሚኖራቸው የመጨረሻው ጨዋታ ለመካፈል መሆኑ ሲታወቅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከያዙት በርካታ የተጨዋቾች ቁጥር አንፃር በምትካቸው ሌላ እንደማይጠሩም ተሰምቷል
አቡበከር ኑሪ- ጅማአባጅፋር
አብዲሳ ጀማል-አዳማ ከተማ

 

ረመዳን የሱፍ- ወልቂጤ ከተማ