ዜናዎች

የብሔራዊ ቡድን የሸገር ዝግጅት ዛሬ ተጠናቋል !

የብሔራዊ ቡድን የሸገር ዝግጅት ዛሬ ተጠናቋል !

የሳምንት ዝግጅቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ይገለፃል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባቱ እና ረዳቶቻቸው የሁለተኛው ምዕራፍ የአንድ ሳምንት ቅደመ ዝግጅታቸውን ዛሬ አጠናቀዋል። የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን አዲስ ንድፈ ሃሳብ መሠረት ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያው ምዕራፍ ለሶስት ቀናት በጅማ የትውውቅ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። በካፍ አካዳሚ መቀመጫቸውን አድርገው ለአንድ ሳምንት በዘለቀው የዝግጅት ጊዜ ውስጥ ጥሪ ከተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ 28 ተጨዋቾች 24 ተጨዋቾች ተገኝተዋል። የፋሲል ከነማ አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ልምምዱን ያደረገ ሲሆን አምሳሉ፣ ሽመክት፣ያሬድ እና ሀብታሙ በእረፍት አለመገኛታቸው ይታውቃል።ለአንድ ሳምንት የቆውን የዝግጅት ጊዜ በተመለከተ እና ቀጣይ የባህርዳር ዝግጅትን ጋር ተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አሰልጣኞቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ማዘጋጀታቸው ታውቋል