ዜናዎች

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ከክለቡ መለያየቱን አስታወቀ !- ከአደጋው በኃላ የጅምናዚየም እንቅስቃሴ ጀምሯል !

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የ33 ዓመቱ ፓትሪክ ማታስ ከአንድ ወር በፊት ከደረሰበት  አሰቃቂ የመኪና አደጋ በኃላ  አገግሞ  እንደተናገረው  በቀጣይ ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር  እንደማይቀጥልና ከክለቡ መለያየቱን አስታውቋል።
ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታስ ከአንድ ወር በፊት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ሙሉ ቤተሰቡን መጎዳቱ ይታወሳል። ተጨዋቾቹ ከአደጋው በኋላ  የመላው  ቤተሰቡ ሕይወት መትረፉ ዕድለኛ መሆኑን በመግለጽ ለራሱ እና ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የህክምና ወጪ የዕርዳታ ጥሪ ማቅረቡም አይዘነጋም። ማታሲ ለጠየቀው የዕርዳታ ጥሪ ኬኒያዊያን አፋጣኝ ምላሽ የሰጡት ሲሆን የህክምና ወጪውን ሙሉ ለሙሉ ተሸፍኖለት  በአደጋው የተጎዱት ሚስቱን እና ልጆቹ በተሳካ ሁኔታ የቀዶ ጥገና አከናውነው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ተዘግቧል።
ማታሲ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ጤናማ ቢሆንም አደጋው የተረፉትን ቤተሰቡን መንከባከብ እና ከቤተሰቡ አጠገብ መሆን እንደሚፈልግ ተናግሮ በአሁኑ ሰዓት በጂምናዚየም ቀላል እንቅስቃሴ  መጀመሩንና አቋሙን እንደሚመለስ ተናግሯል።
ፓትሪክ ማታሲ ለሞዛርት ስፖርት እንደተናገረው ከቅዱስ ጊዮርጊስ  ክላብ ጋር የኮንትራቱ ጊዜው ከሶስት ወር በኃላ በOctober 2021 እንደሚጠናቀቅ እና ከፈረሰኞቹ ጋር በቀጣይ አመት እንደማይቀጥል ለክለቡ ማሳወቁንም ተናግሯል።