ዜናዎች

የቅዱሱ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ገ/ሚካኤል በደቡብ አፍሪካ የነበረው ቆይታ ባለመሳካቱ ወደ ሀገሩ ተመለሰ! !

ከሳምንታት  በፊት ከደቡብ አፍሪካው የስዋቶ  ከተማ ክለብ ከሆነው  ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር   የሙክራ ጊዜ ለማድረግ ወደ  ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች  አማኑኤል ገ/ሚካኤል የሙከራ ጊዜው   ቆይታ ባለመሳካቱ ወደ ሀገሩ  መመለሱ ከክለቡ አካባቢ ለኢትዮኪክ የደረሱ መረጃ ያመለክታሉ።

የአማኑኤል ገ/ሚካኤልን  የመጓዙን መረጃ   ቀድመን  ካስነበብን   በቀናቶች ልዩነት ወደ ደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የ Pre-seasons (የቅድመ  ዝግጅት)  የሙክራ ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ስፍራው የመራው አማኑኤል ከክለቡ ጋር የሁለት ሳምንታት ቆይታ አድርጓል ።

ይሁንና አማኑኤል በክለቡ የትላንትናው ልምምድ  ላይ በልምምድ ሜዳው ስፍራ  እንዳልነበረ እና ከስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር  የነበረው  የሙከራ ጊዜው  መቋረጡን  መረጃዎች ለኢትዮ ኪክ  ጠቁመዋል።

በዚህ መሠረት አማኑኤል   ትላንት ምሽት ወደ  ኢትዮጵያ መመለሱ ሲሰማ  ይኸው መረጃ የደረሳቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብም   በከፍተኛ ክፍያ የአማኑኤልን  ውሉን ለማረዘም እየጠበቁም  እንደሆነ  ታውቋል።

እንደሚታወሰው ከወራቶች በፊት ከደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል በተቃራኒው በምን በኩል እንደሆነ ሳይታወቅ  ከደቡብ አፍሪካው  ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የሙክራ ጊዜ ለማድረግ  መጓዙ አይዘነጋም።

ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)

#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን

tiktok.com/@ethiokick

#በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

#በኢንስታግራም ገጻችንን :-

https://www.instagram.com/ethio_ki

🔛ድረ ገጻችንን :-

Home page