ዜናዎች

ለሻምፒዮኖቹ የአንድ ቢሊዮን ብር የማሰባሰብ ዝግጅት ዛሬ በሸራተን ይጀመራል!

የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ - ፋሲል ከነማ
የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ – የፋሲል ከነማ
የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በሸራተን አዲስ ሆቴል ”ስፖርት ለኢትዮጵያ ሕብረት” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የቴሌቶን ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 17/2013  ከ11:00 ይጀመራል።  ለሻምፒዮኖቹ የአንድ ቢሊዮን ብር የማሰባሰብ  የቴሌቶን ፕሮግራሙ  በቀጣይ  በሶስት ዙር የሚያደርግ ይሆናል ።
የቴሌቶን ፕሮግራሙ ዋና ዓላማ  ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን  በፋይናንስ አቅም ጠንካራ ለማድረግና ለመጭዎቹ ተከታታይ አመታት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ መድረክ አንፀባራቂ ቡድን ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ፕሮግራሙ  በቀጣይ ቀናት በንጉስ እራት ታጅቦ በውቢቷ ባህርዳር እንዲሁም በታሪካዊቷ ከተማ ጎንደር በአፄ ፋሲል አብያተ መንግስታት ግቢ የሚቀጥል  ይሆናል።