ዜናዎች

– የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና የነገው የኢትዮጵያ ጨዋታ የሰዓት ለውጥ ተደረገ !

ቀሪዎቹ የሶስት  የጨዋታ መርሐ ግብር
በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ቀጣዮቹን የምድብ አላፊዎች የሚታወቁበት የቀሪዎቹ የሶስት ጨዋታዎች የጨዋታ መርሐ ግብር በኩል የሰዓት ለውጥ ተደረጓል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ መካከል የሚደረገው የነገ ጨዋታ በቅድሚያ 10:00 ሰአት እንዲደረግ መርሐ ግብር ወጥቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተሻሻለው የውድድር ሰዓት በ8:00 ሰአት የሚደረግ ይሆናል።
በወድድሩ መርሐ ግብር መሠረት ሐሙስ ዕረፍት ሆኖ ዓርብ ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡ ኃላፊ ይታወቃል። ቀጣይ  የመጨረሻው ሁለት የምድቡ ጨዋታዎች ደግሞ ቅዳሜ የሚደረግ ይሆናል። በቅዳሜ መርሐግብር ዮጋንዳ ከታንዛኒያ እንዲሁም ጅቡቲ ከደቡብ ሱዳን የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል
የምድብ ኃላፊ የሚታወቅበት የደረጃ ሰንጠረዡ