አፍሪካ ዜናዎች

የምሽቱን ተጠባቂ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ሙያዊ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተመድበዋል!

May be an image of 10 people and text
በኮትዲቫር አዘጋጅነት እየተከናወነ በሚገኝ የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ከምሽቱ 2 :00 ሰዓት ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉን ተጠባቂ የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከኬኒያዊ ባልደረባቸው ሚኬል አሜንጋ ጋር በአንድነት በመሆን የቴልኒክ ጥናት ክፍል ላይ ተመድበዋል።
የምሽቱን ተጠባቂ ጨዋታ ደግሞ ግብፃዊያኑ አሚን መሐመድ አሚን በመሐል ዳኝነት ሲመሩ መሀሙድ አህመድ ከማል እና አህመድ ሆሳም ታሃ በረዳትነት እንዲሁም ሱዳናዊው መሀሙድ አሊ ሙሀሙድ አራተኛ ዳኛ በመሆን ጨዋታውን የሚዳኙት እንደሚሆን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-