በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በ17 ጎሎች ሁለተኛ የጎል አስቆጣሪው ሙጂብ ቃሲም በዛሬው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን ሁለት ለባዶ ሲያሸንፍ ሁለቱንም ጎሎች አስቆጥሯል።ከጨዋታው በኃላ ሙጂብ ቃሲም ከሱፐርስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሮ የተለየ ደስታ የገለፀበት ምክንያት ?
“ያው እኛ ውጤቱን እንፈልገዋለን ። እየተጫወትን ያለነው ለዋንጫ ነው። ሁሉንም ጨዋታ በትኩረት ነው እየጫወትን ያለነውና ፤ ለዋንጫ እየሄድክ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ጎል ማስቆጠር ትልቅ ነገር ነው። በዛ ላይ አንድ ለባዶ አስተማማኝ አይደለም ። በኃላ ግን ሰአቱም እየሄደ ነው ፤ ሁለተኛም ጎል ስለሆነ ለዛም ነው ደስ ያለኝ።
ከጎል በኃላ ሰብሰብ ብለው ስላወሩት ነገር
” እያወራን የነበረው ትንሽ ከብዶን ነበር። እነሱ ሰው ለሰው ነበር ይዘውን እየተጫወቱ የነበሩት። እናም እነሱ ወደⷛላ ተመልሰው ነበር ሲጫወቱ የነበረው። ክፍተት ለማግኘት መመካከር ስለነበረብን ለዛ ነው የቡድን ስራውን የተሻለ ለማድረግ የተነጋገርነው።
እስካሁን 17 ጎሎች በማስቆጠር ከአቡበከር ጋር ልዩነቱ ሶስት ጎሎች ስለመሆኑ
” እኔ የመጀመሪያው ዓለማዬ ዋንጫ ማንሳቱ ላይ ነው።ምክንያቱም ለሶስት ዓመት ዋንጫ አጥተናል። ያጣንባቸው መንገዶችም ደግሞ በጣም ቀላል በሆኑ አጋጣሚዎች ነው ፤ እና የመጀመሪያው ዓላማዬ ዋንጫ ነው እንደ ተጨዋች ደግም ጎልም እያስቆጠርኩ ነው ፤ከአቡኪ ጋር አንድ ላይ በመሆን የተሻለ ጎል አስቆጥሬ እኔም በጎል አስቆጣሪነት የተሻለ ነገር አደርጋለሁ ብሎ አስባለሁ። ኢህሽ አላህ ይሆናል ።
የመስመር ተጨዋቾች ነበሩ ጎሎቹኔ ያቀበሉትና ይህንን ልምምድ ቦታስ ማዘውተራቸው በተመለከተ
“አሰልጣኛችን ያሰራናል ። አንዳንዴ እንደዚህ ዓይነት ስራዎችን እንሰራለን። ብዙ ጨዋታዎች አይተህ ከሆነ ከመሥመር የሚነሱ ነውና ይህም ደግሞ ልምምድ ላይ የሚሰሩት ነው ወደ ሜዳ የተተጎረጎሙት።