ቸርነት ጉግሳ-ወላይታ ዲቻ
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ዘንድሮ የተሳካ ዘመን ነበረ – የቀረንን ጨዋታ አሸንፈን ትንሽ ከፍ ለማለት ነው የምናስበው ” ቸርነት ጉግሳ

ወላይታ ዲቻ
ወላይታ ዲቻ
የ25ኛው ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ባህርዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። የማሸነፊያ ጎሎቹን አማካዮ ቸርነት ጉግሳ በ55ኛ እና 76ኛው አስቆጥሮ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 5 አድርሷል።  በአማካይ ቦታው ላይ እና በጨዋታው ሁለት ጎሎች ያስቆጠረው ቸርነት ጉግሳ ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
እንኳን ደስ ያለህ
” አመሠግናለሁ “
ስለ ጨዋታው….
” ጨዋታው እንደጠበቅነው አሪፍ ነበር። ጥሩ ይሆናል ብለን ነበረ የገባነው አሪፍ ሆኖ አግኝተነዋል”
ከጨዋታው በፊት ባህርዳርን እናሸንፋለን ብለው አስበው ከነበረ ?
” አዎ እኛ የገባነው አቻ ምንም አይጠቅመንም ነበረ። አሸንፈን ትንሽ ከፍ ብለን ለመጨረስ ነበር የምናስበው የቀረንንም ጨዋታ አሸንፈን ትንሽ ከፍ ለማለት ነው የምናስበው “
በሁለት አሰልጣኝ የውድድር ዓመቱን ክለቡን ያሰለጠኑት፤ በአዲሱ አሰልጣኝ የተለወጠ ነገር ስለመኖሩ?
“ማለት….መጀመሪያ አካባቢ ትንሽ ድክመቶች ነበሩ። የተሰጠንን ነገር አለመተግበር ፣ ችላ ብሎ ቶሎ የመርካት ነገሮች ነበሩ። ይህንን ነገሮች ከአዲሱ አሰልጣኛችን ጋር እሱ የሚሰጠንን እየተገበርን ያሉንን ነገሮች እያስተካከልን እዚህ ደርሰናል”
አሰልጣኝ ዘላለም ጥሩ ከሚባሉ የቡድኑ ተጨዋቾች አንድ ቸርነት ነው ብሎሏል ፣ በቀጣይ ምን ፍላጎት አለው ፣ ከ23አመት በታች ፣ ብሔራዊ ቡድን መጠራት ?
” ማለት ያው ያለው ነገር….. ጊዜው ይደርሳል (በፈገግታ) ከጊዜው ጋር እንሄዳለን ብዬ አስባለሁ ….”
ሁለተኛውን ጎል ሲያስቆጥር ደጉ ነበር የሰጠው ይህን በተመለከተ አስተያየቱ ?
” አዎ…ከደጉ ጋይ ይህንን ነገር ብዙ ጊዜ እንተገብር ነበረ። እስካሁን ባለን የሁለት አመት ቆይታዎች ይህንን ነገር ተደጋጋሚ ጨዋታዎች ላይ እንተገብረው ነበረ ፣ ዛሬ ተሳክቶልናል ብዬ አስባለሁ “
ነገ ወንድሙ ሽመክት ዋንጫ ያነሳል እሱ ከአንተነህ ጋር እዚህ ነወ፣ ለቤተሰባቸው የተሳካ ዘመን ነበረ?
“አዎ ዘንድሮ የተሳካ ዘመን ነበረ  ( በፈገግታ)”