ዜናዎች

ዓፄዎቹ የቅዱስ ጊዮርጊሱን አብዱልከሪም መሐመድ (ተርሙኔተር) አስፈርመዋል!

አብዱልከሪም መሐመድ (ተርሙኔተር)
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ አስቀድሞ ወደ ዝውውር ገቢያው የገባ ቢሆንም ከተጫዋቾች ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ  ያደረገው ዝውውር ይፋ  አልነበረም።  አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ለማስፈረም ከቦርድ አመራሮች ጋር በመሆን ለ2014 ዓ.ም የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከእንየው ካሳሁን ጋር ባለመስማማታቸው የተለያዩት አሰልጣኙ አብዱልከሪም መሐመድን የመጀመሪያ ፊርማ አድርገዋል።
በቀኝ መስመር የተከላካይ ቦታ የሚጫዎተው አብዱልከሪም መሐመድ ደቡብ ፖሊስ ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ቡና ክለቦች እና በብሔራዊ ቡድን የተጫዎተ ሲሆን አሁን ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አፄዎቹ ቤት ሁለት አመት በሚያቆይ ውል ፊርማውን አኑሯል።
@ፋሲል ከነማ