ዜናዎች

” ዓላማችን ታዳጊዎችን ያላቸውን ችሎታ አውጥተው በአውሮፓ እና አሜሪካ ሊጎች ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች በማድረግ ነው” – ሳምሶን ሳምሱንግ (ፊደል አካዳሚ)

ሳምሶን ወጣቶችን በማሰልጠን ተግባር ላይ

ለኢትዮጵያ ለታዳጊዎች ታላቅ የምስራች የሆነውና ወጣቾች በሚወዱት የእግርኳስ ስፖርት መሠረታዊ የእግር ኳስ ስልጠናን እያገኙ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ታላላቅ ሊጎች እንዲጫወቱ ለማድረግ ፊደል የወጣቶች የእግር ኳስ አካዳሚ (Feedel Youth Football Academy) (FYFA) ታላቅ የምስራች ይዞ በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የወደፊት የእግርኳስ ኮከቦችን ለማፍራት በከፍተኛ አቅም ስራውን የጀመረው ፊደል የወጣቶች የእግር ኳስ አካዳሚ ነገ የመጀመሪያ የስካውትንግ ፕሮግራሙን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋል።

የፌደል የወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ ከ5 አመት እስከ 22 አመት ለሆኑ ወንድ ተጫዋቾች እና ሴት ተጫዋቾች ስልጠና እየሰጠ አካዳሚው በስካውቲንግ ባለሙያዎች ግምገማ የተመረጡ ታዳጊዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ግንኙነት ከታላላቅ ሊጎች ጋር ያገናኛል።

የፊደል ወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅ ከሆነው ሳሙኤል ኢትዮ ኪክ ቆይታ አድርገናል

ሳምሶን ሳምሱንግ የፊደል አካዳሚ ባለቤት

ኢትዮኪክ :– የታዳዎች አካዳሚ በኢትዮጵያ ጀምራችኋል እስቲ ስለ አካዳሚው እና አጠቃላይ መረጃ ብትነግረኝ ?

ሳምሶን :- በቅድሚያ ይህንን ዕድል በማግኘታችኘየን በፊደል አከዳሚ ስም ማመስገን እፈልጋለሁ ። ስለ አካዳሚያችን ከመናገሬ በፊት ራሴን በጥቂቱ ላስተዋውቅ።ስሜ ሳምሶን ሳምሱንግ እባላለሁ። ናይጄሪያዊ ስሆን የእግር ኳስ ተጨዋች ነበርኩ አሁንም እጫወታለሁ ። ወደ እዚህ ቢዝነስ ከመግባቴ በፊት ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጨዋች የነበረኩ ሲሆን ከአምስት ዓመት በፊት በጣሊያን ሴሪያ ቢ ይወዳደር ለነበረው ካርቢካሲዮን ክለብ ተጫውቻለሁ ። እንዲሁም ከሁለት አመት በፊት ደግሞ በኢትዮጵያ ሊግ ለሲዳማ ቡና ተጫውቸየቻለሁ። በአውሮፓ የኢስቶንያ ሊግ ጨምሮ የተለያዩ ሊጎች በውሰት አጫጭር ወራቶች የመጫወት ዕድል አጋጥሞኛል። እንዳልኩት ከሁለት አመት በፊት ኮቪድ ሲጀምር አካባቢ ግን በጉዳት ምክንያት እግር ኳስ መጫወቱን ትቼ ቀጥታ ወደ እግርኳስ ቢዝነሱ ነው ገባሁ።

ኢትዮኪክ :- ስለ እግርኳስ ቢዝነሰህ የታዳጊዎች አካዳሚ ስሙን እና ከተመሠረተ ምን ያህል ዓመት እንደሆነው ብትገልጽልኝ ?

ሳምሶን:- የአካዳሚያችን ስሙ ፊደል አካዳሚ ( Feed football l.Academy ) ይባላል። የጀመርነው ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን ከስፖርት ኮሚሽን ፍቃድ አግኝተናል ፣ እንዲሁም ከፌዴሬሽኑም ተቀባይነት ለአንድ ዓመት ተጨዋቾች ይዘን እየሰራን ነው።

ኢትዮኪክ :- የታዳጊዎች አካዳሚ በኢትዮዽያ ለመመሥረት ዋናው ምክንያት እና ዓላማህ ያደረከው?

ሳምሶን :- የእኛ ዓላማችን ኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ በርካታ እግርኳስ ችሎታ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች አሉ። ዋነኛው ዓላማችን እነዚህ ታዳጊዎች ያላቸውን ችሎታ የበለጠ አውጥተው እንዲያዳብሩ እና ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች በማድረግ የሀገሪቱን እግር ኳስ ማገዝ ነው። በኢትዮዽያም ሆነ በአፍሪካ ብዙ ጊዜ ታዳጊዎች ችሎታ እያላቸው በሀገሪቱ የእግር ኳስ አስተዳደራዊ ችግሮች ወይም በአካዳሚ ተይዘው ችሎታቸውን እያዳበሩ ዕድልን ባለማግኘታው የእግር ኳስ ችሎታቸውን ማሳየት ሳይችሉ ይቀራሉ። እኔ በአውሮፓ የመጫወት ዕድሉን አግኝቼ ተጠቅሚያለሁ።በኢትዮጵያ ደግሞ ተጫውቼ አይቻለሁ ። ለታዳጊዎች ተብሎ የሚሰራ የስካውቲንግ ስራዎች በብዛት የሉም ወይም አልተለመዱም ። ለዚህም ነው ታዳጊዎች ችሎታውን እንዲያሳዩ ይህነ አካዳሚ ለመጀመር የፈለኩት።
ኢትዮጵያን የመረጥኩት ባለቤቴ ኢትዮጵያዊ ናት እኔ ደግሞ በኢትዮጵያ ሊግ ስጫወት በርካታ ችሎታ ያላቸው ታዳሚዎች ዕድል ሳያገኙ ቀርተው ተጠቃሚ ሳይሆኑ ሲቀሩ በመመልከቴ ይህን የፊደል ዋና መስሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ አድርጌ ቅርንጫፎቹ ደግሞ በቀጣይ ወር በታንዛኒያ እንከፍታለን ። በተጨማሪም በናይጄሪያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት በሴኔጋልና ዮጋንዳም ተመሳሳይ ስራዎች ለመስራት አቅደናል ነው ።
በተነጋራችን ላይ ይህንን የታዳዎች አካዳሚ በአጋርነት አብረውን ከአምስት እስከ ስድስት የሚደርሱ አለም አቀፍ ሊንኮች አብረውን አሉ። ከነዚህ መሀል የአሜሪካው “Dream Soccer” አንዱ ነው ። በተጨማሪም በርካታ ክለቦች የአውሮፓ ፣ በቱርክ ፣ በስፔን ከሚገኙ ጋር ግንኙነት አለን።
በጣላያን ዋነኛው የተጨዋችች ኤጀንት ሪያላ ፣ የስፔኑ አላዴ እና ሌሎች ክለቦች ጋር አጋሮች ናቸው። ስለዚህ የእኛ ዓላማ ለታዳሚዎቹ ያላቸውን ችሎት የሚያሳዪበት ዕድል መፍጠር ነው። እግር ኳስ ደግሞ ግንኙነት እና ሊንኮች ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም በፕሮፌሽናል መልኩ የምትከፍላቸው ኮንታንት ክፍያዎች አሉ ። ለምሳሌ በየውድድር ዓመቱ ቢያንስ አምስት ወጣቶችን ለማቅረብ እና ታላላቅ የስካውቲንግ ገምጋሚዎች ማቅረብ አለብን ። እንደ ኤሲ ሚላን ፣ኢንተር ሚላን ፣ ጁቬንቱስ የመሳሰሉት ክለቦች።
ስለዚህ በየዓመቱ contact fee በመክፈል የስካውቲንግ ምልመላው ላይ ተጨዋቾች እናቀርባለን።

ኢትዮኪክ :- የአካዳሚው የሚቀበላቸው ታዳሚዎች የዕድሜ ገደብ ?

ሳምሶን :- የዕድሜ በተመለከተ ሁለት ነገሮች ነው የተቀመጡት። የዕድሜ ገደብ 1ኛው በአካዳሚ ለሚገቡ እና 2ኛው ለነው የዓርብ ፕሮግራም ለሚካሄደው የተጨዋቾች መረጣ ፕሮግራም በሚል በሁለት ለይተነዋል።

ስለዚህ ዓርብ ታህሳስ 1 /2014 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ለምናዘጋጀው የስካውትንግ ፕሮግራም የዕድሜ ገደብ ከ17 ዓመት እስከ 23 ዓመት በሚል ሲሆን ይኸም እንዲሁ ከ17 -19 ዓመት እና ከ20 – 23 ዓመት በሚል በሁለት ለይተነዋል። ነገር ግን ለአካዳሚው የሚገቡት ታዳጊዎች ዕድሜ ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሁለቱም ፆታ ይሆናል። የስካውቲንግ ምርጫው ላይ ከ17 ዓመት ጀምሮ የሆነው በFIFA ህግ መሠረት ከ17 ዓመት በታች ብቻውን መጓዝ አይችልም በሚለው ሲሆን ለ18 ዓመት የሚቀረቡ ከመሆኑ አንፃር እና ጊዜ ላለመፈጀት በሚለው ሲሆን የ15 ፣ 16፣ አመት ብቻውን መጓዝ ስለማይችል ቤተሰብ አልያም አብሮት የሚጓዝ ሁሌ ስለሚያስፈልግ ነው።

ኢትዮኪክ :- ዓርብ ታህሳስ 1 /2014 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ስለተጋጀው የስካውትንግ ፕሮግራም በደንብ ብትገልፅልን ?

ሳምሶን :- የዓርብ የስካውቲንግ ፕሮግራሙ የመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን 150 ወጣቶች የሚጠበቁበት ይሆናል። ዝግጁቱ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ለሶስት ሰዓታት የሚካሄድ ሲሆን የወጣቶቹን አጠቃላይ አቋም በቀጥታ ቀረፅ እየተገመገሙ የሚታዪ ይሆናል። ይህን የታዳጊዎቹን እንቅስቃሴ እንዲያዮ ከኢትዮጵያ የስካውቲንግ ባለሙያዎች አሰልጣኞች ይገኛሉ። እስከ አምስት የሚደርሱ የተለያዩ አሰልጣኞች ተጨዋቾችን እንዲያዪ እና የእያንዳንዱን ተጨዋች ብቃት በወረቀት የሚያሰፍሩ ይሆናል። ይሄ የመጀመሪያ ያዘጋጀነው ከመሆኑ እና በውጭ የሚገኙት አጋሮቼ አሰልጣኞች በስታዲየም ተገኝተው ታዳጊዎቹን የማየት ፍላጎት ቢኖራቸውም በኮሮና በተለያዩ ምክንያቶች በአሁኑ እኛ ከሰራን በኋላ ውጤቱን አሳውቃቸዋለሁ ። ይነገው ልዪ ፕሮግራም በየአመቱ የሚቀጥል ይሆናል ።

ኢትዮኪክ :- ታዳጊዎቹ እንደተመረጡ ቀጥታ ወደ አውሮፓ የመጫወት እድል ያገኛሉ ማለት ነው ወይስ?

ሳምሶን :– አይ እንደዛማ አይሆንም ። የዓርብ ልዪ ፕሮግሩሙ በተለየ መልኩ የተዘጋጀው እና የተለየ ችሎታ ያላቸው ታዳጊዎች የሚታዮበት ነው ። በዚህ የስካውትንግ ፕሮግራም በተለየ ሁኔታ ችሎታ ያላቸውን እና አውጥተነው በነበረው ማስታወቂያ የተመዘገቡትን በመምረጥ ከእግር ኳስ ኤጀንቶች ጋር ማገናኘት ወደ ገበያ ማምጣት ነው። ተጨዋቾቹ እንደተመረጡ ቀጥታ ወደ ክለብ ይገባሉ ማለት አይደለም።
ተጨዋቾቹ ከተመረጡ በኋላ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት የተለያዪ ግምገማዎ ይደረጋሉ። በነዚህ ወራቶች የተመረጡትን ተጨዋቾች የህክምና ምርመራ ጨምሮ የተለያዩ ግምገማዎች ይደረጋል። በተጨማሪም ለታዳጊዎቹ ስለ አውሮፓ እግር ኳስ እና የስፖርት ዲሲፕሊን አጭር ስልጠናም ይሰጣቸዋል። ምክንያቱም እዚህ ያለው እና እዛ ያለውን ማወቅ ስለሚገባቸው። ስለዘህ አንድ ወጣት በፊደል አካዳሚ ከሆነ በቀላሉ ስለ ተጨዋቹ ለማወቅ እና ለአውሮፓ እና ለአሜሪካ ሊጎች ላሉን ኤጄነቶች ለማስተወቅ ይረዳናል። የተጨዋቾቻን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በቪዲዮ የተደገፈ እና በቀላሉ በአውሮፓ ያሉት ኤጄንቶች የማስታወቂያ መንገድ ነው።

ኢትዮኪክ :- ተጨዋቾቹ ከተመረጡ በኋላ የት ነው ይህንን የግምገማ ሂደቱን የምታደርጉት ?

ሳምሶን :- አሁን የራሳችን ፊደል አካዳሚ ስላለን እዛ ይሆናሉ። ነገር ግን ናይጄሪም እንዲሁ ቅርንጫፍ አለን። አሁን አዚሁ ነው የሚሆኑት ለዛም ነው አካዳሚ ያለን። በርግጥ ይሄን ጉዳይ የሚለወጥ ይሆናል የተለየ አጭር ስልጠና የሚገኙበት ሁኔታ ሲኖር ወደ ናይጄሪያ የሚጓዙ ሊሆንም ይችላል።

ኢትዮኪክ :- ወደ አካዳው ለሚመጡ ታዳጊዎች የክፍያው ሁኔታ በተመለከተ እንዴት ነው ?

ሳምሶን :- ክፍያው በተመለከተ እኛ የምንፈልገው ዓይነት ታዳጊ ከሆነ ወጪው ሁሉ በአካዳሚው ይሸፍናል። ነገር ግን ተጨዋቹ አማካይ ተጨዋች ከሆነ ለምዝገባ እሰከ 2000 ብር የሚከፍል ይሆናል።

ኢትዮኪክ :- ወጣቶች ወደ አካዳሚው መግባት ቢፈልጉ እንዴት ነው ሊያገኟችሁ የሚችሉት ?

ሳምሶን :- ማንኛውም ሰው (Feedel Youth Football Academy (FYFA) በድረገፃችን ፣በፌስቡክ እና ኢንስትግራም ገፃችን ማግኘት ይችላል።

  • ኢትዮኪክ :- አመሰግናለሁ ስለነበረን ቆይታ ።

ሳምሶን :- ድጋሚ ኢትዮኪክ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

 

One thought on “” ዓላማችን ታዳጊዎችን ያላቸውን ችሎታ አውጥተው በአውሮፓ እና አሜሪካ ሊጎች ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች በማድረግ ነው” – ሳምሶን ሳምሱንግ (ፊደል አካዳሚ)

Comments are closed.