የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት የወቅቱ ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ዛሬ ወሎ ሠፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው በዋነኝነት የማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ጨዋታን በተመለከተ ጉዳዮች ያተኮሩ ቢሆንም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሰበታ ከተማ ጋር የነበራቸውን የስምምነት ሂደትና ተያያዥ ጥያቄዎች ዙረያ በዛሬው መግለጫ ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
እንደሚታወሰው አሰልጣኝ ውበቱ በ2012 መጀመሪያ ወራት አካባቢ የሁለት ዓመታት ውል ከሰበታ ጋር ተፈራርመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ብሄራዊ ቡድኑን እንዲያሰለጥኑ 2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ጥሪ ሲያቀርብላቸው፣ ጥሪውን ተቀብለው፥ ለ2 አመታት ተስማምተው ፈረሙ። የሰበታ ከተማ ጥያቄ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ያልሰሩበትን የአንድ አመት (የ2013ዓ/ም) የፊርማ ክፍያ የመለሱ ሲሆን አሰልጣኝ ውበቱ ከኢ/እ/ፌ ጋር “በቃል ደረጃ” ብቻ እንደሚከፈላቸው መነጋገራቸውን አምነዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይህንን ማድረግ አለመቻሉን ተከትሎ፣ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁለቱም አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።
ሌላው በዛሬው መግለጫ ከተነሱት የብሔራዊ ቡድኑ ጉዳዮች መካከል የመጨረሻዎቹ ሁለቴ ጨዋታዎች እና ቡድኑ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንዲያልፍ በአጠቃላይ የተሰሩ ሥራዎች ምን ነበሩ በሚለው ጉዳይ በሁለቱም አካላት ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኩል የግብ ጠባቂውን ተክለማርያም ሻንቆ ጉዳይ በተመለከተ ለማብራራት እሞክረዋል። አሰልጣኙ እንዳሉት ግብ ጠባቂው በሶስት ጨዋታ ብቻ ጎል የገባበት ፣ በሶስት ጨዋታ ላይ ደግሞ አልተቆጠረበትም ሰለዚህ ጎል ሲገባበት የምንቀይር ከሆነ ትልቅ ስህተት በሚል በማብራራት ለማስረዳት ሞክረዋል።በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በርካታ ብሔራዊ ቡድኑን የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበው ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት የወቅቱ ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ምላሽ ሰጥተዋል።