ዜናዎች

ዋልያዎቹ  ከጋና ጋር በአቻ ውጤት በመለያየታቸው የቡድኑ አባላት መደሰታቸውን ከደቡብ አፍሪካ ተዘግቧል !

በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዚምቧቤ እና ከጋና ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ ምንም እንኳ ከምድቧ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ባትችልም ዛሬ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዋን  በደቡብ አፍሪካ ኦርላንዶ ስታዲየም አድርጋ በአቻ ውጤት አጠናቃለች።
በጨዋታው የጋናው አንድሬ አዮ በ23 ደቂቃ የመጀመሪያ ጎል ቢያስቆጥሩም በመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮጵያ በተጋጣሚዋ ላይ አቻ  በመሆን የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት ለመወጥ ሞክራለች።
 በአንፃሩ በሁለተኛው አጋማሽ ዋልያዎቹ ወደ ጎል በመቅረብ የተሻሉ ነበሩ። በዚህም በ72ኛው ደቂቃ አምበሉ ጌታነህ ከበደ የአቻነት ጎል ማስቆጠር ችሏል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ  ደቡብ አፍሪካ ከዚምቧቤ ጋር ዛሬ የምታደርገው ጨዋታ ውጤት ሳይካተት ምድቡን በ10 ነጥብ ስትመራ  ፣ጋና በተመሳሳይ 10ነጥብ  እና በጎል ክፍያ ተበልጣ ሁለተኛ ኢትዮጵያ ሶስተኛ  ዚምባብዌ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ከጨዋታው በኋላ ኢትዮ ኪክ መረጃ አቀባይ  ከደቡብ አፍሪካ ተጨዋቾቹን ወደ ሆቴል በሚሄዱበት አውቶብስ  ውስጥ  እንዳነጋገራቸው  ምንም እንኳ የዓለም ዋንጫ የመለፍ ዕድሉ ባይኖርም በዛሬው ውጤት መደስታቸውን  ተናግረው ፣ ውጤቱ ለቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ  ተሳትፎ ትልቅ ልምድ እንሚስጥ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታቸውን  የፊታችን እሁድ ህዳር 5/2014ዓ.ም ከ ዚምቧቡዌ ጋር ሀራሬ ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።