ዜናዎች

ዋልያዎቹ ነገ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከዚምባቡዌ ጋር ያደርጋሉ!

 

በኳታሩ የ2022 የአለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በጆሃንስበርግ ኦርላንዶ ስታዲየም ባለፈው ማክሰኞ ከጋና አቻው ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት የተለያየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ጨዋታውን ነገ (እሁድ) ከዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለማድረግ ሀራሬ ይገኛል።

በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው አለም ዋንጫ ከአፍሪካ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በምድብ G ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዚምቧቤ እና ከጋና ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎች አድርጎ ገና በጊዜ መውደቋን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ብሔራዊ በድን ከሌላኛው የምድቡ ተሰናባች ክለብ የዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድን ጋር ነገ ከሰአት ሀራሬ ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምንም እንኳ ከምድቡ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ባይችልም ባለፈው ማክሰኞ ከጋና ጋር ያሳየው የጨዋታ እንቅስቃሴ እና የ 1 ለ 1 የአቻ ውጤት የዓለም ዋንጫ የማለፍ ዕድል ያላትን ጋናን ጭንቀት ውስጥ እንድትባ አድርጓታል።

በአንፃሩ በምድቡ ደቡብ አፍሪካ በ5 ጨዋታ አራቱን አሸንፋ በአንዱ አቻ በመውጣት በ13 ነጥብ የማለፍ ተስፋዋን ያሰፋች ሲሆን ጋና በአምስት ጨዋታ ሶስቱን አሸንፋ በአንዱ ተሸንፋ  ከኢትዮጵያ ጋር ደግሞ በአቻ ውጤት በመለያየቷ  በ10 ነጥብ ነገ  ለማለፍ ታላቁን ፍልሚያ በሜዳዋ ከምድቡ መሪ ደቡብ አፍሪካ ጋር  ታደርጋለች። ጋና ነገ በሜዳዋ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ እንዲጠበቅ አድርጎታል። 

 

One thought on “ዋልያዎቹ ነገ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከዚምባቡዌ ጋር ያደርጋሉ!

  1. ምንም እንኳን ዋሊያዎቹ ለአለም ዋንጫ ማለፍ ባይችሉም ይህ ውድድር ከምንም ጊዜ በላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ጥሩ የውድድር ጊዜ ነበር እኔ እሁንም የውበቱ ቡድን በትላንቱ ጨዋታ አምስት ተጨዋቾችን ቀይሮ መግባቱ ውድድሩ የአንድ ወር ጊዜ እየቀረው ምርጥ አስራንዱን ተጨዋቾች አለመለየቱ ትልቅ ችግር ውስጥ እንዳይገባ ሰጋለው የነገው ጨዋታ የክብር በመሆኑ አሸንፎ እንደሚወጣ እርግጠኛ ነኝ መልካም ዕድል ለዋሊያዎቹ

Comments are closed.