ዜናዎች

ዋልያዎቹ ለቻን ቻምፒዮና ነገ ወድድሩ አዘጋጅ – አልጄሪያ ያመራሉ!

 

በአልጄርያ አስተናጋጅነት ከጥር 5/2015 – ጥር 27/2015 ድረስ በሚካሄደውና የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ከሚሳተፉት 18 ሀገራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዱ እንደሆነ  መዘገቡ ይታወሳል።

በምድብ ሀ ከአስተናጋጇ አልጄርያ ፣ ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ የቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ወደ ሞሮኮ  በማቅናቱ ይታወሳል።

ብሔራዊ  ቡድኑ በሞሮኮ የነበረው ቆይታ  እግርኳስ ፌዴሬሽ  እንደተሸፈነለት ሲታወቅ  ከነገ ጀምሮ ወደ አልጄሪያ ሲያቀና ደግሞ ከሶስት ተጨዋቾች በቀር ለ23 ተጨዋቾች እና ለቡድኑ አሰልጣኞች ካፍ ወጪውን  መሸፈኑ ታውቋል ።ኢ

የኢትዮዽያ የቻን የልዑካን ቡድን  በነገው ዕለት  በራባት  አድርጎ ወደ አልጄሪያ ጉዞውን የሚቀጥል ይሆናል።

መረጃ
በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick

🔛ድረ ገጻችንን :-

Home page

 

 

One thought on “ዋልያዎቹ ለቻን ቻምፒዮና ነገ ወድድሩ አዘጋጅ – አልጄሪያ ያመራሉ!

Comments are closed.