
በመክፈቻ ቀን ጨዋታ ከኤርትራ አቻቸው ጋር 3 ለ 3 አቻ የተለያየው አዘጋጇ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለቀጣይ ጨዋታ ዛሬ ልምምዱን አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ረፋድ ለሁለት ሰዓት የፈጀ የልምምድ መርሐግብሩን ማድረጉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክቷል።በወጣው መርሐ ግብር መሠረት በነገው ጨዋታ ቡሩንዲ ከ ኤርትራ የሚያደረግት አንድ ጨዋታ ብቻ ይካሄዳል። በውድድሩ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ የሴካፋ ጨዋታውን በመጪው ዓርብ ሐምሌ 16 ከቡሩንዲ አቻው ጋር ያደርጋል።
Pic @EFF