አትሌቲክስ ዜናዎች

– ወደ ቶኪዮ ዛሬ ተጓዥ ከሆነው ሁለተኛ ዙር ውስጥ ሦስት ሰዎች ከኤርፖርት ተመላሽ ሆነዋል!

በቶኪዮ 2020/2021 ኦሎምፒክ ኢትዮዽያን አትሌቲክስ የሚወክሉ እና የሁለተኛ ዙር ተጓዞች ዛሬ ምሽት ወደ ጃፓን አምርተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ከሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገፁ ይፋ ካደረገው ተጓዥ ስም ዝርዝር ውስጥ ሦስት የልዑካን አባላት ኦሎምፒክ ለመሄድ ኤርፓርት ደርሰው ከኤርፓት ተመላሽ ተደርገዋል ። በፌዴሬሽን ብዙም ግልፅ ባልሆነው አሰራር አትሌት አላያም የህክምና ባለሞያ ወይም ልዑካን ወደ ቶኪዮ መሄዱን አልያም አለመሄዱን የሚያውቀው ኤርፓርት ውስጥ ከገባ በኋላ ነው ።
ይህውም የኦሎፒክ ኮሚቴ ተወካይ የሆነው ሰው ለተጓዥ አክርቴሽን እና ፓስፓርታቸውን ከኤርፓርት ውስጥ ሆኖ አንድ ተጓዡ ውስጥ ከገባ በኋላ መሄዱን አልያም አለመሄዱን የሚያሳውቀው  ። አትሌትም  አልያም  አሰልጣኝ ወይም የልዑካን ቡድን እስከዚያች ደቂቃ ድረስ በጭንቀት ውስጥ ሆኖ ይጠባበቃል ማለት ነው። በዚህ አሰራር መሠረት  ሶስት ተጓዥ ሰዎች  ኤርፓርት ደርሰው ከኤርፓት ተመላሽ ሆነዋል።
ተመላሽ የሆኑት፦
➖1ኛ ) የቡድኑ ዋና ዶክተር አያሌውም ጥላሁን ለ8ወር ከአትሌቶቹ ጋር ቆይተው ሊጓዙ ኤርፓርት ከደረሱ በኋላ እንዳማይሄዱ የሳቸው ጉዞ ሌላ ቀን እንደሆነ ተነግሯቸው ተመልሰዋል። ዶክተር አያሌው ” የምለው የለኝም” ብለዋል በስፍራው ለነበረው ለመረጃው ባለቤት ኢትዮ-ራነር
ዶክተር አያሌው ጥላሁን

 

➖ 2ኛ ) አሰልጣኝ ኢሳ ሼቦም ያንተ ጊዜ በ29 ነው ተብሎ ተመላሽ ሆኗል።
➖3ኛ ) በሄንግሎ ማጣሪያ በ3000 ሜ መሰናክል ሶስተኛ የወጣው አትሌት ፌደረሽኑ ስሙን ለኦሎፒክ ኮሚቴ ያስተላለፈው አትሌት ሀይለማሪያም አማረም በቅጥል ስሙ አባ ደፋር ስምህ የለም ተብሎ ከኤርፓርት ውስጥ ተመልሷል።
በዚህም መሰረት ፌደረሽኑ ይሄዳሉ ካላቸው 12 ሰዎች ውስጥ ሶስት ተቀንሰው ዘጠኝ የተጓዙ ሲሆን ከኦሎፒኩ በኩል ሁለት ልኡክ ተጓዥ እንዳሉ ኢትዮ-ራነር ለማወቅ ችሏል።
@ኢትዮ-ራነር