ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ከጨዋታው ግለት አንፃር ውጤቱ ጥሩ ነው ” ምክትል አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን (ባህር ዳር ከተማ )

የ19ኛው ሳምንት የምሽቱ ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ከባህዳር አቻቸው ጋር ባደረጉት ጨዋታ አንድ እኩል አቻ አጠናቀዋል ። የባህርዳሩ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በጨዋታ አልተገኘም። የባህርዳር ከተማን  በጨዋታው  ይዞ የገባም ምክትል አሠልጣኙ   ታደሰ ጥላሁን ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ  ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የሚፈልጉትን ውጤት ስለማግኘታቸው ?
በተወሰነ መልኩ የምንፈልገውን አግኝተናል ማለት ይቻላል። ግን ይዘን የመጣነውን እንቅስቃሴ ለመተግበር የጨዋታው ቴምፓ እንዳልከው ጉልበት የተቀላቀለበት ስለነበረ የምንፈለገውን ነገር ማግኘት አልቻልንም። እኛ የኳስ ፍሰቱን ጠብቀን በተለመደው አጨዋወት ውጤታማ ሆነን ለመውጣት ነበር ያሰብነው። የቻልነውን ጥረናል እንግዲህ በአቻ ውጤት እንደአያችሁት አልቋል ። ጥሩ ነው የምንለው ።
የጨዋታ እንቅስቃሴ እና በድሬዳዋዎች ስለተፈጠረባቸው የአጨዋወት ጫና ?
“አዎ!  የኛ ልጆች ኳስ ሲይዞ የመዘግየቱ ሁኔታ ለነሱ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። ሌላው እኛ ሜዳ ላይ ሆነን የምንነካካቸው አብዛኞቹ ነገሮች በስህተቶች የተሞሉ ነበሩ እንዳየኸው ። ስለዚል ያንን ለመቅረፍ የተነጋገርነው ነገር በተወሰነ ለመተግበር አልቻሉም ።የእኛ ልጆች ፍፁም ቅጣት ምቱም ፤ ቅጣት ምቱ ሲገኝ ቶሎ የራሳችንን ሜዳ ለቀን ወደ እነሱ ሜዳ ሄደናል። ብቻ እንድንጫወት የተነጋገርበትን ባለመተግራቸው ጎልም ተቆጥሮብናል። አብዛኛው ነገር ግን በጨዋታ ፍልሰቱ ጥሩ ነገር ታይቷል።
ስለዚህ ውጤቱ ጥሩ ነው ?
ከጨዋታው ግለት አንፃር ውጤቱ ጥሩ ነው ውጤት ነው።