ዜናዎች

“ከኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል የከተማው ተወካይ ክለብ ስትሆኑ አስተዳደሩ አቀባበልና ዕውቅና ይሰጣል”-ኮሚሽነር ዳዊት ትርፉ

በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር  የሚሰለጥነው እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድቡ በአንደኝነት ለሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ  ሽልማት ተበረከተለት ። ወልዲያ ከተማ በምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታውን እያካሄደ ያለውና በ38 ነጥብ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በመጀመሪያ ዙር አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቁና በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  እንዲገባ ለማበረታታትና ለመደገፍ ሲባል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን  የ386,000 ( ሶስት መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ ብር ) ሽልማት ተበርክቶለታል  ።

ክከተማው አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን የተበረክተው የማበረታቻ ሽልማቱ በየደረጃው ላሉ የክለቡ አባላት  የተበረከተ  ሲሆን  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳዊት ትርፉ በስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ባደረጉት ንግግር  ” የከተማውን ን በመወከል  ከአራት ዐመት በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ምድባችሁን በመምራት ውጤት እያስመዘገባችሁ በመሆኑ ትኩረት እንድናደርግ አድርጋችውናል ለዚህም ክብር ይገባችዋል” ብለዋል  በመቅጠልም  ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ዳዊት እንደትናግሩት ” በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስትጫወቱ ማየት የከተማ አስተዳደሩ እና ነዋሪ ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ ለዚህ ድል ስትበቁና ከተማውን ከኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል ሶስተኛው የከተማው ተወካይ ክለብ ስትሆኑ አስተዳደሩ ከማንም ያልተናነሰ አቀባበልና ዕውቅና ይሰጣል ” ሲሉም ቃል ገብተዋል

ምድብ ለ ሁለተኛ ዙር ጨዋታውን እያካሄደ ያለውና በ38 ነጥብ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ  አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር እና አምበሉ ከድር አዩ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን እዚህ ድረስ በመምጣት የተደረገላቸውን ማበረታቻ ሽልማት ፣ ድጋፍና የቀጣይ አቅጣጫ በክለቡ አባላት ስም በማመስገን በቀሪ ጨዋታዎችም አሸናፊ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመግባት ነዋሪውን ህዝብና ከተማ አስተዳደሩን እንደሚያኮሩ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ሁለተኛ ዙር ጨዋታውን በወልዲያ እያካሄደ ሲሆን እስካሁን አራት ጨዋታዎች በማድረግ ሶስቱን ሲያሸንፍ አንዱን አቻ በመውጣት ምንም ግብ ሳይቆጠርበት 7 ጎል በማስቆጠር ምድቡን በ38 ነጥብ ከተከታዩ አምበርቾ ክለብ በ7 ነጥብ ቀድሞ እየመራ ይገኛል ሲል የከተማው አስተዳደር እዝብ ግንኙነት ዘግቧል።