ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሊቪዥን ስርጭት ሽፋን አያገኙም!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር በሃዋሳ ከተማ ከ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ውድድሩ በቀጥታ የሱፐር ስፖርት ሽፋን እያገኘ እስከ 24ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስለሆነም አክሲዬን ማህበሩ ከመልቲቾይዝ አፍሪካ(ዲኤስቲቪ) ጋር ባለው የብሮድካስት ውሉ መሰረት በአመቱ የሚተላለፉ ጨዋታዎች ጋር በተያያዘ በሃዋሳ ከተማ የሚደረጉ ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሊቪዥን ስርጭት ሽፋን አያገኙም። ጨዋታዎቹ በቀጥታ ስርጭት ባይተላለፉም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ በኩል ግን የቪድዮ ቀረፃ  ተከናውኖ ለአስፈላጊው አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል።  በተጨማሪም የሊግ ውድድሩ የመጨረሻ ሳምንታት ጨዋታዎች በቀጥታ ስርጭት በሱፐርስፖርት የሚተላለፉ መሆኑን አክሲዮን ማህበሩ አሳውቋል።