ዜናዎች

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየታቸው ተሰማ !

Coach Frank Nuttall
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ  ከወራት በፊት የከለቡ ዋና አሰልጣኝ አደርጎ ከሾመው እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ጋር መለያየቱ እየተዘገበ ይገኛል።
ከደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት ከወራቶች በፊት የተለያየው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር እንግሊዛዊውን አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል ።
በአንፃሩ ፈረንሰኞቹ  ከእንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል  ጋር የአጭር ጊዜ ስምምነት እንደነበራቸው ሲገለፅ  አሰልጣኙም  በአጭር ጊዜ በቆይታቸው እንደተጠበቁት ባለመሆናቸው አሁን ከቡድኑ ጋር እንደተለያዩ እየተዘገበ ይገኛል።