በ2013 የቤትኪንግ የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃትን ካሳዮ ወጣት ተጨዋቾች አንዱ በወንድማገኝ ሃይሉ ዛሬ ለሃዋሳ ሶስተኛውን እና የመጨረሻውን ጎል አስቆጥሯል። በDSTV ከጨዋታው በፊት ቆይታ ያደረገውና የወደፊት ፍላጎቱን የተናገረው ወንድማገኝ ሃይሉ ከጨዋታው በኋላም የጨዋታውን በተመለከተ ከሱፐር ስፓርት ጋዜጠኛ ሰኢድ ኪያር ጋር ቆይታ አድርጓል።
የውድድር ዓመቱን ሲጀምር እና አሁን ሲጨርስ በዚህ መልኩ ጠብቆት ነበር?
” እንደ ተጨዋች ሁሌ ስኬታማ መሆንን ነው የማስበው።ማሸነፍን ሁሌም አስበን ነው የምንገባው ወደ ሜዳ። የመጨረሻውን በስኬት ጨርሰነዋል። ደስ ብሎኛል በአጠቃላይ”
ከወጣቶቹ እና ልምድ ካላቸው ጋር መጫወቱ መግባባት ነበረው ?
” አዎ በጣም። ከ” ቢ” ጀምሮ አብረን የነበረን ልጆች ነን አብነን ያለነው፣ እንዲሁም ልምድ ያላቸውም አሉ። በጣም መግባባት አለ ቡድናችን ውስጥ። ያ ነገር ደግሞ ረድቶናል’
ስለ ቀጣይ ፍላጎቱና ዓላማው ?
” እንደ ተጨዋች ትልቅ ነገር ነው የማስበው ። የወጣት ቡድንም ከተሳካልኝ እሰየው ነው። እኔም ከዚህ በላይም ማሰብ አለብኝ እና ፣ የፕሪምየር ሊገን ትልቁን ኮከብነት ማሸነፍ እፈልጋለሁ”
እስካሁን ያስቆጠራቸውን ጎሎች ትልቅ አስተዋጽኦ ላደረገ አበርክት ብትባል ለማን ታበረክታለህ ለሚለው ?
” ለአሰልጣኜ ሊሰጠው ደስ ይለኛል። ከ “ቢ” ጀምሮ ላሳደገኝም አሁንም ላለው ለዋናው ለሙልዬ እና ለብርሃኑ (ፈየራ) ብሰጠው ደስ ይለኛል”
የሚያድግ ልጅ ነዉ። ትኩረት ቢደረግበት ምርጥ የአጥቂ አማካይ ለብሔራዊ ቡድን ማገኘታችን ነዉ።
በርታ!